በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የጻፉት ሐሳብ ምንጩ አምላክ እንደሆነ ተናግረዋል። እስቲ የሚከተሉትን ምሳሌዎች ልብ በል፦

  •  ንጉሥ ዳዊት፦ “የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ተናገረ፤ ቃሉ በአንደበቴ ላይ ነበረ።”—2 ሳሙኤል 23:1, 2

  •  ነቢዩ ኢሳይያስ፦ “የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል።”—ኢሳይያስ 22:15

  •  ሐዋርያው ዮሐንስ፦ “አምላክ ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውና በእሱ የተገለጠው ራእይ ይህ ነው።”—ራእይ 1:1