በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የተፈጥሮ አደጋዎች የአምላክ ቁጣ ናቸው?

የተፈጥሮ አደጋዎች የአምላክ ቁጣ ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በዛሬው ጊዜ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎችን የሚያመጣው አምላክ እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ አያስተምርም። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው የምናገኛቸው የአምላክ የፍርድ እርምጃዎች ከተፈጥሮ አደጋዎች በእጅጉ የተለዩ ናቸው።

  1. አምላክ የሚያጠፋው በጅምላ ሳይሆን እየመረጠ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “ሰው የውጭውን ገጽታ ያያል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ያያል” ይላል።—1 ሳሙኤል 16:7

  2. ይሖዋ የሰዎችን ልብ ማንበብ ስለሚችል እርምጃ የሚወስደው ጥፋት በሚገባቸው ሰዎች ላይ ብቻ ነው።—ዘፍጥረት 18:23-32

  3. አምላክ፣ እሱን የሚሰሙ ሰዎች ከጥፋቱ መዳን እንዲችሉ አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ ያስነግራል።

ከዚህ በተለየ መልኩ የተፈጥሮ አደጋዎች የሚከሰቱት የተወሰኑ የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ብቻ አሳይተው አሊያም ያለምንም ማስጠንቀቂያ ነው፤ በተጨማሪም እገሌ ከእገሌ ሳይሉ ይገድላሉ ወይም ለአካል ጉዳት ይዳርጋሉ። የሰው ልጆች፣ አካባቢያቸውን በማበላሸት እንዲሁም ለመሬት መንቀጥቀጥና ለጎርፍ በተጋለጡ ወይም መጥፎ የአየር ንብረት ባለባቸው ቦታዎች ላይ ቤቶችንና ሕንጻዎችን በመገንባት በተወሰነ መጠንም ቢሆን እነዚህ አደጋዎች የሚያስከትሉት ጥፋት የከፋ እንዲሆን አስተዋጽኦ አድርገዋል።