በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ጋብቻን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ጋብቻን በተመለከተ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መንግሥታት ጋብቻን በተመለከተ ሕግጋት ከማውጣታቸው ከብዙ ጊዜያት በፊት ፈጣሪያችን ጋብቻ ሊመራበት የሚገባውን ሥርዓት ሰጥቷል። የመጀመሪያው የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።” (ዘፍጥረት 2:24) በቫይን የተዘጋጀው ኤክስፖዚተሪ ዲክሽነሪ ኦቭ ቢብሊካል ዎርድስ “ሚስት” የሚለው የዕብራይስጥ ቃል “አንስታይ ፆታ ያላትን ሰብዓዊ ፍጥረት ያመለክታል” ብሏል። ኢየሱስም በጋብቻ የሚጣመሩት “ወንድና ሴት” መሆን እንዳለባቸው ገልጿል።—ማቴዎስ 19:4

 እንግዲያው የአምላክ ዓላማ፣ ጋብቻ በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚመሠረት ዘላቂ ወዳጅነት እንዲሆን ነበር። ስለዚህ ወንዶችና ሴቶች የተፈጠሩት አንዳቸው የሌላኛውን ስሜታዊና ፆታዊ ፍላጎቶች በማርካት ለትዳር ጓደኛቸው ማሟያ እንዲሆኑ ተደርገው ነው፤ አንድ ወንድና አንዲት ሴት የሚፈጥሩት ይህ ጥምረት ልጆችን ለማፍራትም ያስችላል።