በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች ስለሚፈጽሙት ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች ስለሚፈጽሙት ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ሁሉም ዘሮች በአምላክ ፊት እኩል በመሆናቸው የተለያየ ዘር ያላቸው ወንድና ሴት የሚፈጽሙት ጋብቻ በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው። መጽሐፍ ቅዱስ ‘አምላክ ለየትኛውም ብሔር እንደማያዳላ’ ይናገራል።​—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35

 ስለ ዘር እኩልነትና ስለ ትዳር የሚናገሩ ሌሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ሐሳቦችን እንመልከት፦

የሁሉም ዘሮች መገኛ አንድ ነው

 ሁሉም የሰው ዘሮች የተገኙት ከመጀመሪያው ሰው ማለትም ከአዳም እና መጽሐፍ ቅዱስ “የሕያዋን ሁሉ እናት” ብሎ ከሚጠራት ከሚስቱ ከሔዋን ነው። (ዘፍጥረት 3:20) በመሆኑም አምላክ “የሰውን ወገኖች በሙሉ ከአንድ ሰው [እንደፈጠረ]” መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 17:26) የሰው ልጆች በሙሉ ዘራቸው ምንም ይሁን ምን የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው። ይሁንና በምትኖርበት አካባቢ የዘር ጥላቻና የመደብ ልዩነት በስፋት የሚታዩ ቢሆንስ?

ጥበበኛ ሰዎች ‘ይመካከራሉ’

 የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች የሚመሠርቱት ትዳር በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ቢኖረውም በዚህ የሚስማሙት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። (ኢሳይያስ 55:8, 9) ከአንተ የተለየ ዘር ያላትን ሴት ለማግባት አስበህ ከሆነ በሚከተሉት ሐሳቦች ላይ አንድ ላይ መወያየታችሁ አስፈላጊ ነው፦

  •   ከማኅበረሰቡና ከቤተሰብ የሚያጋጥማችሁን ተጽዕኖ መቋቋም የምትችሉት እንዴት ነው?

  •   ልጆቻችሁ የሚያጋጥማቸውን ጭፍን ጥላቻ መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?

 በዚህ መልኩ ‘መመካከራችሁ’ ትዳራችሁ ስኬታማ እንዲሆን ሊረዳችሁ ይችላል።​—ምሳሌ 13:10፤ 21:5