በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?

ለሚደርስብን መከራ ተጠያቂው አምላክ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ መከራ የሚያመጣው አምላክ እንዳልሆነ አበክሮ ይገልጻል! በሰው ልጆች ላይ መከራ እንዲደርስ የይሖዋ አምላክ ዓላማ አልነበረም። ይሁን እንጂ የመጀመሪያዎቹ ባልና ሚስት በአምላክ አገዛዝ ላይ በማመፅ መልካምና ክፉ የሆነውን በተመለከተ የራሳቸውን መሥፈርት አወጡ። ለአምላክ ጀርባቸውን መስጠታቸው ያስከተለባቸውንም መዘዝ ለመቀበል ተገደዱ።

 እነሱ ባደረጉት መጥፎ ውሳኔ የተነሳ ዛሬም በእኛ ላይ መከራ እየደረሰብን ይገኛል። ሆኖም በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው መከራ መንስኤው በጭራሽ አምላክ አይደለም።

 መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ማንም ሰው ፈተና በሚደርስበት ጊዜ ‘አምላክ እየፈተነኝ ነው’ አይበል። ምክንያቱም አምላክ በክፉ ነገሮች ሊፈተን አይችልም፤ እሱ ራሱም ማንንም አይፈትንም።” (ያዕቆብ 1:13) በአምላክ ዘንድ ሞገስ ያገኙ ሰዎችን ጨምሮ መከራ በማንም ሰው ላይ ሊደርስ ይችላል።