በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

“የሕይወት መጽሐፍ” ውስጥ የተጻፈው የእነማን ስም ነው?

“የሕይወት መጽሐፍ” ውስጥ የተጻፈው የእነማን ስም ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 “የሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል” እና “የመታሰቢያ መጽሐፍ” ተብሎ የተጠራው ‘የሕይወት መጽሐፍ’ የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይዟል። (ራእይ 3:5፤ 20:12፤ ሚልክያስ 3:16) አምላክ በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የሚጻፈው ማን እንደሆነ የሚወስነው ለእሱ ያሳዩትን ታማኝነት መሠረት በማድረግ ነው።​—ዮሐንስ 3:16፤ 1 ዮሐንስ 5:3

 አምላክ የሰው ዘር “ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ” የታማኝ አገልጋዮቹን ስም በመጽሐፍ ላይ የመጻፍ ያህል በአእምሮው ውስጥ ይዟል። (ራእይ 17:8) ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ውስጥ የተጻፈው የመጀመሪያው ታማኝ ሰው አቤል ሳይሆን አይቀርም። (ዕብራውያን 11:4) ይሖዋ ’የእሱ የሆኑትን የሚያውቅ’ አፍቃሪ አምላክ ስለሆነ በዚህ መጽሐፍ ላይ የሰፈሩ ሰዎችን በስም ብቻ ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዳቸውን ያውቃቸዋል።​—2 ጢሞቴዎስ 2:19፤ 1 ዮሐንስ 4:8

አንድ ሰው ስሙ “ከሕይወት መጽሐፍ” ላይ ሊደመሰስ ይችላል?

 አዎ። አምላክ በጥንቷ እስራኤል የነበሩ ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎችን አስመልክቶ “የበደለኝን ሁሉ ከመጽሐፌ እደመስሰዋለሁ” በማለት ተናግሯል። (ዘፀአት 32:33) ታማኝ መሆናችንን ካስመሠከርን ግን ‘ከሕይወት መጽሐፍ ጥቅልል’ ላይ ስማችን አይደመሰስም።​—ራእይ 20:12