በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል?

ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል?

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 እንዲህ ማድረግ ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ በኢየሱስ ስም ለአምላክ ብቻ መጸለይ እንዳለብን ይገልጽልናል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።’” (ማቴዎስ 6:9 አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅዱሳን፣ ወደ መላእክት ወይም ከአምላክ ውጪ ወደ ሌላ አካል እንዲጸልዩ አላዘዛቸውም።

 በተጨማሪም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14:6 ..) አምላክ አማላጅ እንዲሆን አድርጎ የሾመው ኢየሱስን ብቻ ነው።​—ዕብራውያን 7:25

ወደ አምላክ መጸለዬ እንዳለ ሆኖ ወደ ቅዱሳንም ጭምር ብጸልይስ?

 አምላክ አሥርቱን ትእዛዛት ሲሰጥ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ . . . ቀናተኛ አምላክ ነኝ” ብሏል። (ዘፀአት 20:5 ..) ይሁንና አምላክ “ቀናተኛ” የሆነው እንዴት ነው? የማጥኛ ጽሑፍ ያለው አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻው ላይ እንደሚናገረው “ቀናተኛ” ሲባል “እርሱን ብቻ ማምለክን ይጠይቃል።” በመሆኑም አምላክ ጸሎትን ጨምሮ ከአምልኮ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ነገሮች ለእሱ ብቻ እንድናቀርብ ይፈልጋል።—ኢሳይያስ 48:11

 ከእሱ ውጪ ሌላው ቀርቶ ለቅዱሳንና ለመላእክትም ብንጸልይ አምላክ ያዝንብናል። ሐዋርያው ዮሐንስ ለአንድ መልአክ የአምልኮ ስግደት ሊያቀርብለት ሲል መልአኩ እንደሚከተለው በማለት አስቁሞታል፦ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ።”​—ራእይ 19:10 ..