በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኢየሱስ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው ብቻ ነበር?

ኢየሱስ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው ብቻ ነበር?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ኢየሱስ እንዲሁ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው ብቻ አልነበረም። እስከ ዛሬ ከኖሩ ሰዎች ሁሉ የበለጠ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደረ ሰው ነው። ቀጥሎ የተጠቀሱት ታዋቂ የታሪክ ምሁራንና የታሪክ ጸሐፊዎች ስለ ኢየሱስ ምን እንዳሉ ተመልከት፦

 “የናዝሬቱ ኢየሱስ . . . በታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሰው እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም።”—ኸርበርት ጆርጅ ዌልስ፣ እንግሊዛዊ የታሪክ ምሁር

 “በታሪክ ውስጥ [የኢየሱስን] ያህል በብዙ ሰዎች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ሰው የለም፤ ወደፊትም የበለጠ ተጽዕኖ ማሳደሩን ይቀጥላል።”—ኬኔት ስካት ላቱሬት፣ አሜሪካዊ የታሪክ ምሁርና ደራሲ

 ኢየሱስ እስከ ዛሬ ከኖሩት ጥሩ ሰዎች ሁሉ የበለጠ በሰው ልጆች ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው ለምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በአንድ ወቅት ኢየሱስ የሚቀርባቸውን ተከታዮቹን፣ እሱ ማን እንደሆነ እንደሚያስቡ ጠይቋቸው ነበር፤ አንዱ የኢየሱስ ተከታይ “አንተ መሲሑ፣ የሕያው አምላክ ልጅ ነህ” በማለት ትክክለኛ መልስ ሰጥቷል።—ማቴዎስ 16:16