በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አጋንንት በእርግጥ አሉ?

አጋንንት በእርግጥ አሉ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

አጋንንት በእርግጥ አሉ። አጋንንት በአምላክ ላይ ያመፁ መንፈሳዊ ፍጥረታት ሲሆኑ ‘ኃጢአት የሠሩ መላእክት’ ተብለው ተጠርተዋል። (2 ጴጥሮስ 2:4) ራሱን ጋኔን ያደረገው የመጀመሪያው መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን መልአክ ‘የአጋንንት አለቃ’ በማለት ይጠራዋል።—ማቴዎስ 12:24, 26

በኖኅ ዘመን የነበረው ዓመፅ

መጽሐፍ ቅዱስ በኖኅ ዘመን ከደረሰው የጥፋት ውኃ በፊት መላእክት እንዳመፁ ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ።” (ዘፍጥረት 6:2) እነዚህ ክፉ ወይም ዓመፀኛ መላእክት ከሴቶች ጋር የፆታ ግንኙነት ለመፈጸም ሲሉ በሰማይ የነበረውን “ትክክለኛ መኖሪያቸውን” ትተው የሰው አካል ለበሱ።​—⁠ይሁዳ 6

የጥፋት ውኃው ሲመጣ ዓመፀኞቹ መላእክት የለበሱትን ሰብዓዊ አካል በመተው ወደ ሰማይ ተመለሱ። ይሁንና አምላክ ከቤተሰቡ አባረራቸው። በተጨማሪም ድጋሚ ሰብዓዊ አካል እንዳይለብሱ በመከልከል ቀጣቸው።​—⁠ኤፌሶን 6:11, 12