በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

አንድ ወንድና አንዲት ሴት የሚዋደዱ እስከሆነ ድረስ ሳይጋቡ አብረው ቢኖሩ ምን ችግር አለው?

አንድ ወንድና አንዲት ሴት የሚዋደዱ እስከሆነ ድረስ ሳይጋቡ አብረው ቢኖሩ ምን ችግር አለው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ “አምላክ ሴሰኞችን . . . ይፈርድባቸዋል” በማለት በግልጽ ይናገራል። (ዕብራውያን 13:4) “ሴሰኞች” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ፖርኒያ ሲሆን ይህ ቃል ከጋብቻ በፊት የፆታ ግንኙነት መፈጸምንም ያመለክታል። በመሆኑም ያልተጋቡ ወንድና ሴት ወደፊት ትዳር ለመመሥረት ቢያስቡም እንኳ ሳይጋቡ አብረው መኖራቸው በአምላክ ፊት ስህተት ነው።

ይሁንና እነዚህ ሰዎች በጣም የሚዋደዱ ከሆነስ? አምላክ የፆታ ግንኙነት ከመፈጸማቸው በፊት እንዲጋቡ ይጠብቅባቸዋል። ማፍቀር እንድንችል አድርጎ የፈጠረን አምላክ ነው። ዋነኛው የአምላክ ባሕርይም ፍቅር ነው። (1 ዮሐንስ 4:8) በመሆኑም የፆታ ግንኙነት መፈጸም የሚችሉት የተጋቡ ወንድና ሴት ብቻ እንደሆኑ የገለጸበት በቂ ምክንያት አለው።