በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በኢየሱስ ስም መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

በኢየሱስ ስም መጸለይ ያለብን ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በኢየሱስ ስም መጸለይ ያለብን፣ አምላክ ወደ እሱ እንድንቀርብ የሚፈልገው በኢየሱስ በኩል ብቻ ስለሆነ ነው። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ። በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14:6) በተጨማሪም ኢየሱስ ታማኝ ሐዋርያቱን “እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ አብን ማንኛውንም ነገር ብትጠይቁት በስሜ ይሰጣችኋል” ብሏቸዋል።—ዮሐንስ 16:23

በኢየሱስ ስም ለመጸለይ የሚያነሳሱን ተጨማሪ ምክንያቶች

  •   ለኢየሱስና ለአባቱ ለይሖዋ አክብሮት እንዳለን እናሳያለን።—ፊልጵስዩስ 2:9-11

  •   አምላክ፣ በኢየሱስ ሞት አማካኝነት እኛን ለማዳን ያደረገውን ዝግጅት እንደምንቀበል እናሳያለን።—ማቴዎስ 20:28፤ የሐዋርያት ሥራ 4:12

  •   ኢየሱስ በሰውና በአምላክ መካከል አማላጅ የመሆን ልዩ ቦታ እንዳለው መገንዘባችንን እናሳያለን።—ዕብራውያን 7:25

  •   ኢየሱስ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አቋም እንድናገኝ ሲል ሊቀ ካህናት በመሆን የሚጫወተውን ሚና እንደተቀበልን እናሳያለን።—ዕብራውያን 4:14-16