በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ

አመጣጥ እና ተአማኒነት

መጽሐፍ ቅዱስ ምንድን ነው?

አስደናቂ የሆነውን የአምላክን ቃል ማንበብ ጀምር።

መጽሐፍ ቅዱስ ሰብዓዊ ጥበብ የሚንጸባረቅበት መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ የሚሰጠውን ምሥክርነት ልብ በል።

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክን ሐሳብ የያዘ መጽሐፍ ነው?

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች አምላክ መርቷቸው እንደጻፉ ተናግረዋል። እንዲህ ያሉት ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን የጻፈው ሙሴ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፉት ሰዎች መካከል አንዱ ሙሴ ነው። ለመሆኑ መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ምን ያህል ሰዎች ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስን ማን እንደጻፈው በእርግጠኝነት ማወቅ ይቻላል?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች መጽሐፉን በአምላክ መንፈስ መሪነት እንደጻፉት ይናገራሉ። ይሁንና በውስጡ የያዘው ሐሳብ እውነት መሆኑን ማመን የምንችለው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ተቀይሯል ወይም ተበርዟል?

መጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ መጽሐፍ ከመሆኑ አንጻር መልእክቱ እንዳልተቀየረ እንዴት እርግጠኞች መሆን እንችላለን?

አምላክ ጽንፈ ዓለምን መፍጠር የጀመረው መቼ ነው?

የዚህን ጥያቄ መልስ ለማወቅ “መጀመሪያ” እና “ቀን” የሚሉት ቃላት በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ የተሠራባቸው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ያስፈልጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ከሳይንስ ጋር ይስማማል?

ከሳይንስ አንጻር ስህተት የሆነ ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አለ?

መጽሐፍ ቅዱስ ምድር ጠፍጣፋ እንደሆነች ያስተምራል?

ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ የያዘው ሐሳብ ትክክል ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የነጮች መጽሐፍ ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ትውልድና እድገት የት ነው?

ስለ ኢየሱስ የሚተርኩት ዘገባዎች የተጻፉት መቼ ነው?

ወንጌሎች የተጻፉት ኢየሱስ ከሞተ ከምን ያህል ጊዜ በኋላ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና መረዳት

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ቁልፉ ምንድን ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ውድ መልእክት መረዳት ትችላለህ።

መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ የሚጋጩ የሚመስሉ ሐሳቦችንና ትርጉማቸውን በትክክል ለመረዳት የሚያስችሉ ነጥቦችን ተመልከት።

የአምላክ ቃል ማን ወይም ምንድን ነው?

ይህ ሐረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከአንድ በላይ ትርጉም አለው።

“ዓይን ስለ ዓይን” ሲባል ምን ማለት ነው?

“ዓይን ስለ ዓይን” የሚለው ሕግ በቀልን ያበረታታል?

አሥርቱ ትእዛዛት ምንድን ናቸው?

አሥርቱ ትእዛዛት የተሰጡት ለማን ነው? ክርስቲያኖች እነዚህን ትእዛዛት ማክበር ይጠበቅባቸዋል?

“ደጉ ሳምራዊ” የሚባለው ምን ዓይነት ሰው ነው?

ኢየሱስ በዚህ ታሪክ በመጠቀም፣ ሰዎች ዘራቸው ወይም ብሔራቸው ምንም ይሁን ምን እንዴት ልንይዛቸው እንደሚገባ ግሩም አድርጎ አስተምሯል።

ኦሪት ምንድን ነው?

ኦሪትን የጻፈው ማን ነው? በኦሪት ውስጥ የሚገኙት ትምህርቶች የማይሻሩና ዘላለማዊ ናቸው?

ትንቢት እና ምልክቶች

ትንቢት ምንድን ነው?

በአምላክ መንፈስ መሪነት የተነገሩ ትንቢቶች በሙሉ ስለ ወደፊቱ ጊዜ የሚናገሩ ናቸው? ላይሆን ይችላል።

ቁጥሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ትርጉም አላቸው? ኒውመሮሎጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ አለው?

አንዳንድ ቁጥሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ምሳሌያዊ ትርጉም አላቸው? ይህስ ከኒውመሮሎጂ የሚለየው እንዴት ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ የዘመን ስሌት መሠረት 1914 ምን የሆነበት ዓመት ነው?

በዳንኤል ምዕራፍ 4 ላይ የተጠቀሰው “ሰባት ዓመት” ከሰው ልጅ አገዛዝ ጋር በተያያዘ አንድ ዓይነት ሁኔታ ሰፍኖ የነበረበትን ዘመን ያመለክታል።

የራእይ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

ይህ መጽሐፍ ራሱ እንደሚገልጸው በውስጡ ያለውን መልእክት የሚያነብቡና ተረድተው ሥራ ላይ የሚያውሉ ሰዎች ደስተኞች ይሆናሉ።

“አልፋና ኦሜጋ” ማን ወይም ምንድን ነው?

ይህ መጠሪያ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ምን ታመለክታለች?

ይህች ለየት ያለች ከተማ በአንተ ላይ ተጽዕኖ የምታሳድረው እንዴት ነው?

በራእይ ምዕራፍ 13 ላይ የተገለጸው ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ ምን ያመለክታል?

አውሬው ሥልጣንና ዙፋን እንዳለው ተገልጿል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያለው ትንቢት ሌላስ የሚገልጸው ነገር አለ?

በራእይ ምዕራፍ 17 ላይ የተጠቀሰው ደማቅ ቀይ አውሬ ምን ያመለክታል?

ይህን አስፈሪ አውሬ ለማወቅ የሚረዱ ስድስት ነጥቦች።

የ666 ትርጉም ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ 666 የተባለው ቁጥርና የአውሬው ምልክት ምን እንደሚያመለክቱ ይነግረናል።

ታላቂቱ ባቢሎን ማን ናት?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አንድ ከተማና አመንዝራ ሴት አድርጎ ይገልጻታል።

የእሳት ሐይቅ ምንድን ነው? ገሃነም ነው? ወይስ ሲኦል?

ኢየሱስ “የሲኦል መክፈቻ” አለው፤ ነገር ግን የእሳት ሐይቅ መክፈቻ አለው?

ሀብታሙ ሰውና አልዓዛር እነማን ናቸው?

ኢየሱስ የተናገረው ምሳሌ ጥሩ ሰዎች ወደ ሰማይ እንደሚሄዱና መጥፎ ሰዎች በሲኦል እሳት እንደሚሠቃዩ ያስተምራል?

የዓለም ፍጻሜ

‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም ‘የመጨረሻው ዘመን’ ምልክት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻዎቹን ቀናት ለይተው የሚያሳውቁ ክንውኖችን አስቀድሞ ነግሮናል፤ እነዚህ ክንውኖች በተመሳሳይ ጊዜ ላይ መፈጸማቸው የመጨረሻዎቹ ቀናት መድረሳቸውን ይጠቁማል።

መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ስለሚኖሩ ሰዎች ባሕርይ እና ምግባር ትንቢት ተናግሯል?

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎች ባሕርይ ይበልጥ እየተበላሸ እንደሚሄድ ትንቢት ተናግሯል።

ታላቁ መከራ ምንድን ነው?

በተለምዶ “የመጨረሻው ዘመን ትንቢቶች” የሚባሉት ትንቢቶች በሰው ልጆች ላይ ስለሚመጣው ታላቅ የመከራ ጊዜ ይናገራሉ። በዚያ ወቅት ምን ይከናወናል?

የአርማጌዶን ጦርነት ምንድን ነው?

አርማጌዶን የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ነው፤ ይህ ቃል ስለሚያመለክተው ጦርነት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሰፊው ተብራርቷል።

ምድር ትጠፋለች?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ያስገርምህ ይሆናል።

የዓለም መጨረሻ የሚመጣው መቼ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ይህ የሚሆንበትን ጊዜ በቀጥታ ይነግረናል?

የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?

የአምላክ መንግሥት ምድርን ሲገዛ ምን ነገሮችን እንደሚያከናውን እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ሰዎች፣ ቦታዎች፣ የተለያዩ ነገሮች

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱ ሴቶች ምን እንማራለን?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ግሩም ባሕርይ ያላቸው ሴቶችንና መጥፎ ሴቶችን ታሪክ አንብብ።

ማርያም የአምላክ እናት ናት?

ቅዱሳን መጻሕፍትም ሆኑ የክርስትና ታሪክ ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ግልጽ መልስ ይዘዋል።

ድንግል ማርያም—መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሷ ምን ይላል?

አንዳንዶች ማርያም ስትፀነስ ጀምሮ ከኃጢአት ነፃ እንደነበረች ይናገራሉ። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ትምህርት ይደግፋል?

መጥምቁ ዮሐንስ ማን ነው?

ዮሐንስ የተናገረው ትንቢታዊ መልእክት፣ ወገኖቹ የሆኑት አይሁዳውያን ተስፋ የተሰጠበትን መሲሕ ማወቅ እንዲችሉ አዘጋጅቷቸዋል።

መግደላዊቷ ማርያም ማን ነበረች?

ስለ እሷ በተለምዶ የሚነገሩት አንዳንድ ሐሳቦች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የላቸውም።

“ሰብአ ሰገል” እነማን ነበሩ? “ኮከቡን” ያዘጋጀው አምላክ ነው?

ከገና ልማዶች ጋር ተያያዥነት ያላቸው በርካታ የተለመዱ አገላለጾች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም።

ዳንኤል ማን ነው?

አምላክ ለዳንኤል በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ስላሉት ነገሮች ራእይ አሳይቶታል።

የቃየን ሚስት ማን ነበረች?

መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ያስችላል።

የኖኅ እና የጥፋት ውኃው ታሪክ እውነተኛ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ ክፉ ሰዎችን ለማጥፋት በውኃ እንደተጠቀመ ይናገራል። መጽሐፍ ቅዱስ ከአምላክ የመጣ ለመሆኑ ምን ማስረጃ አለ?

የቃል ኪዳኑ ታቦት ምንድን ነው?

አምላክ እስራኤላውያንን ታቦቱን እንዲሠሩ አዝዟቸው ነበር። የታቦቱ ዓላማ ምን ነበር?

የቱሪን ከፈን—ኢየሱስ የተገነዘው በዚህ ጨርቅ ነበር?

ከፈኑን በተመለከተ ሦስት ሐሳቦችን መመልከታችን መልሱን ለማግኘት ያስችለናል።

አምላክ የተለያዩ ፍጥረታትን ወደ ሕልውና ለማምጣት በዝግመተ ለውጥ ተጠቅሟል?

ሳይንስ በአንድ የፍጥረት ወገን ሥር በሚመደቡ ፍጥረታት መካከል የተወሰነ ልዩነት ሊኖር እንደሚችል ይናገራል፤ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ሐሳብ አይቃወምም።

ተግባራዊ ጠቀሜታ

መጽሐፍ ቅዱስ ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖረኝ ሊረዳኝ ይችላል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ጥበብ ያዘሉ ምክሮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በቤተሰብ ሕይወታቸው ደስተኛ እንዲሆኑ ረድተዋቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጓደኝነት ምን ይላል?

ጥሩ ጓደኞች በጎ ተጽዕኖ ያሳድሩብናል፤ እንዲሁም የተሻልን ሰዎች እንድንሆን ይረዱናል። ጓደኞችህን በጥንቃቄ ምረጥ!

ወርቃማው ሕግ ምንድን ነው?

ኢየሱስ ወርቃማውን ሕግ በሰጠበት ወቅት እየተናገረ የነበረው በጥቅሉ ሰዎችን እንዴት መያዝ እንዳለብን ብቻ አይደለም፤ ከዚህም ባለፈ ጠላቶቻችንን እንኳ እንዴት ልንይዝ እንደሚገባ እየገለጸ ነበር።

“ጠላቶቻችሁን ውደዱ” ሲባል ምን ማለት ነው?

ኢየሱስ የተናገረው ቀላል ሆኖም ጥልቀት ያለው ሐሳብ በሥራ ላይ ለማዋል ከባድ ሊሆን ይችላል።

ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

ጥበብና ማስተዋል ለማግኘት የሚረዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ስድስት ምክሮች።

ተስፋ የሚሰጥ ነገር ከየት ማግኘት እችላለሁ?

አሁን በሕይወትህ ደስተኛ እንድትሆን፣ የወደፊቱን ጊዜ ደግሞ በተስፋ እንድትጠብቅ የሚረዳህ ነገር ከየት ማግኘት ትችላለህ? እስቲ እምነት የሚጣልበት አንድ የመረጃ ምንጭ እንጠቁምህ።

ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?

ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተወሰደ የሚነገርለት “ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው” የሚለው የተለመደ አባባል የጥቅሱን የተሟላ ሐሳብ የያዘ አባባል አይደለም።

የገንዘብ ችግርና ዕዳ—መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ ይችላል?

ገንዘብ ደስታን ሊገዛ አይችልም፤ ይሁንና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ሊረዱህ የሚችሉ አራት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አሉ።

ከከባድ በሽታ ጋር መኖር—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው እርዳታ አለ?

አዎ! ከባድ በሽታን ለመቋቋም የሚረዱ ሦስት እርምጃዎች እነሆ!

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በቀል ምን ይላል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ምክር ብዙዎች የበቀል ስሜታቸውን እንዲያሸንፉ ረድቷቸዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ቁጣን በተመለከተ ምን ይላል?

መቆጣት ተገቢ የሚሆንበት ጊዜ አለ? እየተናደድክ እንደሆነ ሲሰማህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ጭንቀት ውስጥ ስገባ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?

አምላክ ጭንቀት ውስጥ የገቡ ሰዎችን ለመርዳት የሚጠቀምባቸው ሦስት መንገዶች አሉ።

ሃይማኖት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ወይም አምላክ ደስታ እንድታገኝ ሊረዱህ ይችላሉ?

ከአምላክ ጋር ወዳጅነት መመሥረት የአሁኑንም ሆነ የወደፊት ሕይወትህን ሊያሻሽልልህ የሚችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ መውደድ ምን ይላል?

ኢየሱስ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” ሲል ተናግሯል። ይህ ምን ማለት ነው?