በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?

ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ሲኦል ወይም ሔድስ የሚያመለክቱት ሰዎች በእሳት የሚሠቃዩበትን ቦታ ሳይሆን የሰው ልጆችን መቃብር ነው። ሲኦል የሚገቡት እነማን ናቸው? ጥሩ ሰዎችም ሆነ መጥፎ ሰዎች ሲኦል ይገባሉ። (ኢዮብ 14:13 የ1954 ትርጉም፤ መዝሙር 9:17) መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉም የሰው ልጆች የሚገቡበት ይህ መቃብር “ለሕያዋን ሁሉ [የተመደበ] ስፍራ” እንደሆነ ይናገራል።​—⁠ኢዮብ 30:23

ኢየሱስም እንኳ ሲሞት የሄደው ወደ ሲኦል ነው። ያም ሆኖ አምላክ ከሞት ስላስነሳው ‘በሲኦል አልቀረም።’​—⁠የሐዋርያት ሥራ 2:31, 32 አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሲኦል ለዘላለም ይቀጥላል?

ሲኦል ውስጥ የገቡ ሰዎች ሁሉ ከሲኦል መውጣታቸው አይቀርም፤ ኢየሱስ ከአምላክ ያገኘውን ኃይል ተጠቅሞ ከሞት ያስነሳቸዋል። (ዮሐንስ 5:28, 29፤ የሐዋርያት ሥራ 24:15) ራእይ 20:13 (አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ወደፊት የሚከናወነውን ትንሣኤ አስመልክቶ ሲናገር “ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ውስጥ የነበሩትን ሙታን ሰጡ” ይላል። ሲኦል በውስጡ ያለውን በሙሉ ከሰጠ በኋላ ይወገዳል፤ ከዚያ በኋላ ‘ሞት ስለማይኖር’ ማንም ሰው ሲኦል ውስጥ አይገባም።​—⁠ራእይ 21:3, 4፤ 20:14

ይሁን እንጂ የሞቱ ሰዎች ሁሉ ሲኦል ይገባሉ ማለት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች ኃጢአት ሠርተው ንስሐ ለመግባት ፈቃደኛ እንደማይሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ዕብራውያን 10:26, 27) እንዲህ ያሉ ሰዎች ሲሞቱ የሚገቡት ሲኦል ውስጥ ሳይሆን ገሃነም ውስጥ ነው፤ ገሃነም ዘላለማዊ ጥፋትን ያመለክታል። (ማቴዎስ 5:29, 30) ለምሳሌ ያህል፣ ኢየሱስ በዘመኑ የነበሩት አንዳንድ ግብዝ የሃይማኖት መሪዎች ወደ ገሃነም እንደሚገቡ ተናግሮ ነበር።​—⁠ማቴዎስ 23:27-33