በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ የነጮች መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ የነጮች መጽሐፍ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው በአውሮፓውያን አይደለም። አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጻፍ የተጠቀመው አውሮፓውያንን ሳይሆኑ በመካከለኛው ምሥራቅ የሚኖሩ ሰዎችን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ አንዱ ዘር ከሌላው እንደሚበልጥ አያስተምርም። እንዲያውም እንዲህ ይላል፦ “አምላክ እንደማያዳላ በእርግጥ አስተዋልኩ፤ ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና የጽድቅ ሥራ የሚሠራ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።”—የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35