በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሰዎች ላይ ለሚደርሰው መከራ በሙሉ ተጠያቂው ዲያብሎስ ነው?

በሰዎች ላይ ለሚደርሰው መከራ በሙሉ ተጠያቂው ዲያብሎስ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰይጣን በእውን ያለ አካል እንደሆነና ልክ እንደ አንድ ኃይለኛ የወንጀለኞች መሪ ዓላማውን ለመፈጸም “በሐሰተኛ ምልክቶችና” ‘በክፋት ዘዴ’ እንደሚጠቀም ይገልጻል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሰይጣን “የብርሃን መልአክ ለመምሰል ዘወትር ራሱን ይለዋውጣል” በማለት ይናገራል። (2 ተሰሎንቄ 2:9, 10፤ 2 ቆሮንቶስ 11:14) ዲያብሎስ ያደረሰው ጥፋት የእሱን መኖር ያረጋግጣል።

 ያም ቢሆን በሰዎች ላይ ያለውን መከራ በሙሉ የሚያደርሰው ዲያብሎስ አይደለም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? አምላክ ሰዎችን የፈጠረው ጥሩ ወይም መጥፎ ነገር ማድረግን መምረጥ እንዲችሉ እንዲችሉ አድርጎ ነው። (ኢያሱ 24:15) መጥፎ ውሳኔዎችን ካደረግን መጥፎ ውጤት ማጨዳችን አይቀርም።—ገላትያ 6:7, 8