በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ፈታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ፈታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ምን ማድረግ ትችላለህ?

በመጀመሪያ፣ ጓደኞችህ ምንም አደረጉ ምን፣ አንተ ለምትወስዳቸው እርምጃዎች ተጠያቂው ራስህ መሆንህን አስታውስ።

ሁለተኛ፣ በጣም ፈታኝ የሚሆንብህን ነገር ለይተህ ለማወቅ ሞክር።

ቀጥሎም፣ ‘ፈተናው ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመኝ መቼ ነው?’ ብለህ ራስህን ጠይቅ። (ትምህርት ቤት ስሆን? ሥራ ቦታ ስሆን? ወይስ ሌላ ጊዜ?) ፈታኝ ሁኔታዎች ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥሙህ መቼ እንደሆነ ማወቅህ ከእነዚህ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ለመራቅ ሊረዳህ ይችላል።

አሁን፣ እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተሃል። በቅድሚያ ልትወስደው የሚገባው እርምጃ፣ ፈታኝ የሚሆንብህ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበትን አጋጣሚ መቀነስ ወይም ጭራሹኑ ማስቀረት የምትችልበትን መንገድ መፈለግ ነው። (ምሳሌ፦ ሲጋራ እንድታጨስ የሚገፋፉህ ተማሪዎች የሚያጋጥሙህ ከትምህርት ቤት ስትመለስ ከሆነ ከእነሱ ጋር ላለመገናኘት መንገድ መለወጥ ትችል ይሆናል።) እውነታው፦ ጓደኞችህ እንደሆኑ የምታስባቸው ሰዎች፣ መጥፎ ነገሮችን እንድትፈጽም ጫና የሚያደርጉብህ ከሆነ እውነተኛ ጓደኞች አይደሉም።

ለሚያጋጥሙህ ፈተናዎች እጅ የምትሰጥ ከሆነ ለምኞቶችህ ባሪያ ትሆናለህ

እርግጥ ነው፣ ፈታኝ ከሆኑ ሁኔታዎች በሙሉ መራቅ አትችልም። ፈጽሞ ባልጠበቅኸው ጊዜ ላይ በጣም ፈታኝ የሆነ ሁኔታ ሊያጋጥምህ ይችላል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታዎችን ለመቋቋም ምን ማድረግ አለብህ?

ቁልፉ ዝግጁ መሆን ነው!

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ኢየሱስ ከሥነ ምግባር ጋር በተያያዘ ምን አቋም መውሰድ እንዳለበት ያውቅ ነበር። ምንጊዜም አባቱን ለመታዘዝ ቁርጥ ውሳኔ አድርጎ ነበር። (ዮሐንስ 8:28, 29) እንግዲያው ፈታኝ ሁኔታዎችን ለማሸነፍ ቁልፉ፣ ምን አቋም እንደምትወስድ አስቀድመህ መወሰን ነው።

መልመጃ። ብዙውን ጊዜ የሚያጋጥምህን ፈታኝ ሁኔታ መቋቋም ያለብህ ለምን እንደሆነ የሚገልጹ ሁለት ምክንያቶችን እንዲሁም ፈተናውን ለመቋቋም መውሰድ የምትችላቸውን ሁለት እርምጃዎች ለማሰብ ሞክር።

ሌሎች እንዲቆጣጠሩህ ለምን ትፈቅዳለህ? ትክክል የሆነውን በማድረግ የበሰልክ ሰው መሆንህን አሳይ። (ቆላስይስ 3:5) እንዲሁም ምንጊዜም ይህን ማድረግ እንድትችል አዘውትረህ ጸልይ።—ማቴዎስ 6:13