በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

ጓደኞች ማግኘት ካልቻልኩ ምን ላድርግ?

ጓደኞች ማግኘት ካልቻልኩ ምን ላድርግ?

ምን ማድረግ ትችላለህ?

በመጀመሪያ፣ ጓደኛ ለማድረግ የሚከብዱህ ምን ዓይነት ሰዎች እንደሆኑ ለማሰብ ሞክር።

ዕድሜ፦

 • ከእኩዮቼ

 • በዕድሜ ከሚበልጡኝ ወጣቶች

 • ከትላልቅ ሰዎች

. . . ጋር ጓደኝነት መመሥረት ይከብደኛል።

ችሎታ፦

 • ከስፖርተኞች

 • ልዩ ተሰጥኦ ካላቸው ሰዎች

 • ከተማሩ ሰዎች

. . . ጋር ጓደኝነት መመሥረት ይከብደኛል።

ባሕርይ፦

 • በራሳቸው ከሚተማመኑ

 • ተወዳጅ ከሆኑ

 • ቡድን ካላቸው

. . . ሰዎች ጋር ጓደኝነት መመሥረት ይከብደኛል።

ሁለተኛ፣ ከላይ ከጠቀስካቸው ሰዎች ጋር ስትሆን አብዛኛውን ጊዜ ምን ታደርጋለህ?

 • ከእነሱ ጋር ተመሳሳይ ዝንባሌ ወይም ችሎታ እንዳለኝ አስመስላለሁ።

 • የእነሱን ዝንባሌ ችላ ብዬ የራሴን ብቻ አወራለሁ።

 • ምንም ትንፍሽ ሳልል እቆይና አጋጣሚውን ሳገኝ ሹልክ ብዬ እወጣለሁ።

ሦስተኛ፣ ቅድሚያውን ውሰድ! ሁልጊዜ ሌሎች እንዲቀርቡህ አትጠብቅ፤ አንዳንዴ አንተ ራስህ ቅድሚያውን ወስደህ እነሱን ለመቅረብ ጥረት ማድረግ ይኖርብሃል። (ፊልጵስዩስ 2:4) ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

እኩዮችህ ያልሆኑ ሰዎችንም ለመቅረብ ጥረት አድርግ። እስቲ አስበው፣ በአንተ ዕድሜ ላይ የሚገኙትን ካልሆነ በስተቀር ማንንም ጓደኛ ላለማድረግ ራስህን ገድበህ ስታበቃ ጓደኛ አላገኘሁም ብለህ ብታማርር ምን ይባላል? እንዲህ ማድረግ፣ ዓሦች የሞሉበት ባሕር በከበበው ደሴት ላይ ሆነህ በረሃብ እንደ መሞት ነው!

እናቴ ከአዋቂዎች ጋር ለማውራት ጥረት እንዳደርግ አበረታታችኝ። የሚያመሳስለን ብዙ ነገር እንዳለን ሳውቅ መገረሜ እንደማይቀር ነገረችኝ። ደግሞም ልክ ነበረች፤ አሁን ብዙ ጓደኞች አሉኝ!”—ሄለና፣ 20

ከሌሎች ጋር የመነጋገር ችሎታ አዳብር። ቁልፉ (1) ማዳመጥ፣ (2) ጥያቄ መጠየቅ እና (3) የምታነጋግረውን ሰው ከልብ መቅረብ እንደምትፈልግ ማሳየት ነው።—ያዕቆብ 1:19

ብዙ ከማውራት ይልቅ አዳማጭ ለመሆን እጥራለሁ። ስናገር ደግሞ ስለ ራሴ ላለማውራት ወይም ስለ ሌሎች አፍራሽ ነገር ላለመናገር እሞክራለሁ።”—ሴሬና፣ 18

አንድ ሰው እኔ ስለማላውቀው ነገር ማውራት ከጀመረ አንዳንድ ነገሮችን እንዲያብራራልኝ እጠይቀዋለሁ፤ ይህ ደግሞ ጨዋታው እንዲቀጥል ያደርጋል።”—ጃረድ፣ 21

ዓይናፋር ስለሆንኩ ጭውውት ለመጀመር ይከብደኛል። ጓደኞች ለማፍራት ደግሞ ሌሎችን መቅረብ መቻል አለብህ። ስለዚህ የግዴን አወራ ጀመር።”—ሊያ፣ 16