በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የወጣቶች ጥያቄ

የወላጆቼን መመሪያ ብጥስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

የወላጆቼን መመሪያ ብጥስ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

ችግሩ እንዳይባባስ ምን ልታደርግ ትችላለህ?

እውነቱን ተናገር። አለዚያ ወላጆችህ በአንተ ላይ ያላቸው እምነት ጨርሶ ሊጠፋ ይችላል። ስለዚህ ሐቀኛ ሁን፤ እንዲሁም ጉዳዩን አድበስብሰህ ለማለፍ አትሞክር።ምሳሌ 28:13

  • ለድርጊትህ ሰበብ ከማቅረብ ወይም ጥፋትህን ቀለል አድርገህ ከመናገር ተቆጠብ።

  • የለዘበ መልስ ቍጣን እንደሚያበርድ’ ምንጊዜም አስታውስ።—ምሳሌ 15:1

ይቅርታ ጠይቅ። ወላጆችህን በማስጨነቅህ፣ በማበሳጨትህ ወይም በእነሱ ላይ ጫና በመፍጠርህ በጣም እንዳዘንክ መግለጽህ ተገቢ ከመሆኑም በላይ የሚደርስብህን ቅጣት ሊያቀልልህ ይችላል። ሆኖም የተጸጸትከው ከልብህ መሆን አለበት።

ጥፋትህ የሚያስከትለውን ቅጣት ለመቀበል ፈቃደኛ ሁን። ድርጊትህ ያስከተለውን ውጤት መቀበል የብስለት ምልክት ነው። ማድረግ የምትችለው ከሁሉ የተሻለ ነገር የወላጆችህን አመኔታ መልሰህ ለማግኘት መጣር ነው።ምሳሌ 20:11

ወላጆችህ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ አንተን የመቆጣጠር ኃላፊነት እንዳለባቸው ማስታወስ ይገባሃል። መጽሐፍ ቅዱስ ‘ስለ አባት ትእዛዝ’ እና ‘ስለ እናት ትምህርት’ የሚናገረው ለዚህ ነው።ምሳሌ 6:20

ወላጆችህ ተጨማሪ ነፃነት እንዲሰጡህ ከፈለግህ

  • ያወጧቸውን መመሪያዎች ሁልጊዜ በመታዘዝ የእነሱን አመኔታ አትርፍ።

  • ታዛዥነት የማንነትህ ክፍል እንዲሆን አድርግ፤ ይህም ሲባል ባሕርይህና ያለህ አቋም ታዛዥ መሆንህን የሚያሳይ ሊሆን ይገባል።