በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የወጣቶች ጥያቄ

ወላጆቼ ያወጡትን ሕግ ለመታዘዝ ምን ሊረዳኝ ይችላል?

ወላጆቼ ያወጡትን ሕግ ለመታዘዝ ምን ሊረዳኝ ይችላል?

እኩዮችህ፣ እስከፈለጉበት ሰዓት አምሽተው ቤታቸው ይገቡ፣ ያሻቸውን ይለብሱ ወይም ከጓደኞቻቸው ጋር ወደፈለጉበት ቦታ ባሰኛቸው ሰዓት ይሄዱ ይሆናል። ምናልባት የእነዚህ ልጆች ወላጆች በሥራ ከመጠመዳቸው የተነሳ ልጆቻቸው ምን እንደሚያደርጉ ሳያስተውሉ ቀርተው ሊሆን ይችላል።

ልጅን በዚህ መልኩ ማሳደግ ጥሩ ውጤት እንደማያስገኝ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ምሳሌ 29:15) ዛሬ በዓለም ላይ ለሚታየው የፍቅር መጥፋት ዋነኛው መንስኤ ሰዎች ራስ ወዳድ መሆናቸው ሲሆን ከእነዚህ ሰዎች አብዛኞቹ ቁጥጥር በማይደረግበት ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ናቸው።2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

ደስ ያላቸውን ነገር ሁሉ እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸውን ወጣቶች በማየት ከመቅናት ይልቅ ወላጆችህ መመሪያዎች የሚያወጡልህ ስለሚወዱህና ስለሚያስቡልህ እንደሆነ ለመረዳት ሞክር። እንዲያውም ወላጆችህ ምክንያታዊ የሆኑ ገደቦች ማውጣታቸው የይሖዋ አምላክን ምሳሌ እንደሚከተሉ የሚያሳይ ነው፤ ይሖዋ ለሕዝቡ እንዲህ ብሎ ነበር፦

“አስተምርሃለሁ፤ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ እመክርሃለሁ፤ በዐይኔም እከታተልሃለሁ።”መዝሙር 32:8