በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጋብቻ

የስኬት ቁልፍ

ትዳራችሁ አስደሳች እንዲሆን የአምላክን መመሪያ ተከተሉ

ሁለት ቀላል ጥያቄዎችን በመጠቀም ትዳራችሁን ማሻሻል ትችላላችሁ።

ትዳርን አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትዳርን አስደሳች ማድረግ ስለሚቻልበት መንገድ የሚሰጠው ምክር ጠቃሚ ነው፤ ምክንያቱም ይህን ምክር ያስጻፈው የጋብቻ መሥራች የሆነው ይሖዋ አምላክ ነው።

የቤተሰብ ሕይወትን አስደሳች ለማድረግ የሚረዳ ጥበብ

ባል፣ ሚስት፣ ወላጆችና ልጆች ቤተሰባቸው ደስተኛ እንዲሆን ምን ማድረግ ይችላሉ?

ስኬታማ ቤተሰቦች—ተባብሮ መሥራት

ከባለቤትህ ጋር የትዳር ጓደኛሞች ናችሁ ወይስ ደባል?

የመጀመሪያውን ዓመት የትዳር ሕይወት ስኬታማ ማድረግ

አዲስ ተጋቢዎች ናችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ ትዳራችሁን ለማጠናከር ሊረዳችሁ ይችላል።

ትዕግሥት ማዳበር የሚቻለው እንዴት ነው?

ትዳር ፍጹም ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ጥምረት ስለሆነ የተለያዩ ችግሮች መነሳታቸው አይቀርም። ለስኬታማ ትዳር ትዕግሥት ወሳኝ ነገር ነው።

ለሰመረ ትዳር፦ አክብሮት ማሳየት

በትዳራችሁ ውስጥ መከባበር ጠፍቷል? መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳችሁ ይችላል።

አክብሮት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?

አክብሮት አንዳንድ ጊዜ ብቻ ልናሳየው የሚገባ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለትዳር ወሳኝ የሆነ ባሕርይ ነው። ለትዳር ጓደኛችሁ አክብሮት ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

ለሰመረ ትዳር፦ ፍቅር መግለጽ

ሥራ፣ ውጥረት እንዲሁም የሕይወት ሩጫ ባለትዳሮች በስሜት እንዲራራቁ ሊያደርግ ይችላል። ታዲያ ባለትዳሮች ቀድሞ የነበራቸውን ሞቅ ያለ ፍቅር እንደገና ማቀጣጠል የሚችሉት እንዴት ነው?

አድናቆት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?

ባለትዳሮች አንዳቸው የሌላውን ጥሩ ባሕርይ ለማስተዋልና ለማድነቅ ጥረት የሚያደርጉ ከሆነ ትዳራቸው ጠንካራ ይሆናል። ታዲያ አድናቆት ለማዳበር ምን ሊረዳህ ይችላል?

ፍቅርን መግለጽ የሚቻለው እንዴት ነው?

የትዳር ጓደኛሞች አንዳቸው ለሌላው ፍቅራቸውን መግለጽ የሚችሉት እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ላይ የተመሠረቱ አራት ጠቃሚ ሐሳቦችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የጋብቻን ቃለ መሐላ ጠብቆ መኖር የሚቻለው እንዴት ነው?

ቃለ መሐላን የምትመለከተው ካደረግከው መጥፎ ውሳኔ ጋር ጠፍሮ እንደሚያስር እግር ብረት አድርገህ ነው ወይስ ትዳራችሁ እንዳይናጋ እንደሚያደርግ መልሕቅ?

አንዳችሁ ለሌላው ታማኝ ሁኑ

በትዳር ውስጥ ታማኝ መሆን ሲባል ምንዝር አለመፈጸምን ብቻ ነው የሚያመለክተው?

ሁለተኛ ትዳር እንዲሰምር ማድረግ

በመጀመሪያ ትዳር ወቅት ጨርሶ ያልነበሩ ተፈታታኝ ሁኔታዎች በሁለተኛ ትዳር ላይ ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ታዲያ ሁለተኛ ትዳር የመሠረቱ ባልና ሚስት ሊሳካላቸው የሚችለው እንዴት ነው?

ባሎች—ቤታችሁ ስጋት የሌለበት ቦታ እንዲሆን አድርጉ

አንድ ባል ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ቁሳዊ ነገር ሁሉ ቢያቀርብም እንኳ የቤተሰቡ አባላት ስጋት ሊያድርባቸው ይችላል።

ደስታ የሚያስገኝ መንገድ—ፍቅር

ፍቅር ለደስታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚደረግ ጋብቻን በተመለከተ ምን ይላል?

የጋብቻ ጥምረት አስደሳችና ዘላቂ እንዲሆን ምን መደረግ እንዳለበት ከሁሉ በተሻለ የሚያውቀው የጋብቻ መሥራች የሆነው ፈጣሪ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ከአንድ በላይ ማግባትን ይደግፋል?

ከአንድ በላይ ማግባት እንዲጀመር ያደረገው አምላክ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን እንደሚል መርምር።

የተለያየ ዘር ያላቸው ሰዎች ስለሚፈጽሙት ጋብቻ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ስለ ዘር እኩልነትና ስለ ትዳር የሚገልጹ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦችን እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትዳር ምን ይላል?

ባለትዳሮች የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች የሚከተሉ ከሆነ ከተለያዩ ችግሮች መዳን ወይም ተቋቁመው ማለፍ ይችላሉ።

ጋብቻ እንዲሁ አብሮ ለመኖር የሚደረግ ማኅበራዊ ዝግጅት ነው?

አንድ ባልና ሚስት አምላክ የሰጣቸውን ድርሻ መወጣታቸው ስኬታማና ደስተኛ እንዲሆኑ የሚረዳቸው እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ?

አንድ ሰው ደስተኛ ለመሆን የግድ ማግባት ይኖርበታል?

ትዳር የሌላቸው ክርስቲያኖች ደስተኛ ሊሆኑ ይችላሉ? መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ትዳርን በሚመለከት ምን አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚገባ እንዲሁም ነጠላነትን አስመልክቶ ማን ፍጹም ምሳሌያችን ሊሆን እንደሚችል ይናገራል።

ችግሮች እና መፍትሔያቸው

የትዳር ጓደኛችሁ ያለውን የሚያበሳጭ ጠባይ በአዎንታዊ መንገድ ማየት

የትዳር ጓደኛችሁ ያለው የሚያበሳጭ ጠባይ በመካከላችሁ ግጭት እንዲፈጥር ከመፍቀድ ይልቅ ያንን ጠባይ በአዎንታዊ መንገድ ለማየት ጥረት አድርጉ።

ሥራን ሥራ ቦታ መተው

ሥራችሁ በትዳራችሁ ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ ለማድረግ የሚረዷችሁ አምስት ጠቃሚ ምክሮች።

የቤት ውስጥ ጥቃት ለሚደርስባቸው የሚሆን እርዳታ

የአንቺ ጥፋት እንዳልሆነና ብቻሽን እንዳልሆንሽ አትርሺ።

በትዳር ጓደኛ ላይ የሚሰነዘር ጥቃት መፍትሔው ምን ይሆን?

የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች እጅግ ጠበኛ የሆኑ ሰዎች እንኳ ሳይቀሩ ባሕርያቸውን እንዲለውጡ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ከአማቶች ጋር ተስማምቶ መኖር

ከአማቶቻችሁ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟችሁ ችግሮች በትዳራችሁ ውስጥ ችግር እንዳይፈጥሩ የሚረዷችሁ ሦስት ጠቃሚ ምክሮችን ተመልከቱ።

ከዘመዶቻችሁ ጋር በሰላም መኖር የምትችሉት እንዴት ነው?

ትዳራችሁን ሳትጎዱ ለወላጆቻችሁ አክብሮት ማሳየት ትችላላችሁ።

የአመለካከት ልዩነትን ማስታረቅ

ባለትዳሮች ችግሮችን ፈተው በሰላም መኖር የሚችሉት እንዴት ነው?

የትዳር አጋርሽ ፖርኖግራፊ የሚመለከት ከሆነ

አንድ ባል የፖርኖግራፊ ሱስ ካለበት ሱሱን እንዲያሸንፍ እንዲሁም በትዳራቸው ውስጥ ያለው መተማመን እንዲመለስ ባልና ሚስቱ ተባብረው መሥራት የሚችሉት እንዴት ነው?

ፖርኖግራፊ ትዳራችሁን ሊያናጋው ይችላል

እነዚህ ምክሮች የፖርኖግራፊ ሱስህን ለማሸነፍና ትዳርህና መልሰህ ለማጠናከር ይረዱሃል።

የአመለካከት ልዩነቶችን ማስታረቅ

ከትዳር ጓደኛህ ጋር ፈጽሞ እንደማትጣጣም ተሰምቶህ ያውቃል?

ቂምን መተው የሚቻልበት መንገድ

የትዳር ጓደኛችሁ የፈጸመውን ስህተት ይቅር ለማለት ጥፋቱን አቅልላችሁ መመልከት ወይም ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን ይጠበቅባችኋል?

ስኬታማ ቤተሰቦች—ይቅር ባይ መሆን

በትዳር ጓደኛችሁ አለፍጽምና ላይ ትኩረት ላለማድረግ ምን ሊረዳችሁ ይችላል?

ልጆች ራሳቸውን ችለው መኖር ሲጀምሩ

አንዳንድ ባለትዳሮች ልጆቻቸው አድገው ከቤት ሲወጡ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። ወላጆች በዚህ ወቅት የሚሰማቸውን ስሜት ማሸነፍ የሚችሉት እንዴት ነው?

ቤተሰባችሁ መከራ ሲያጋጥመው

የሚያስፈልጋችሁን እገዛ ከመጠየቅ ወደኋላ አትበሉ።

ቅናት ትዳራችሁን እንዳይበጠብጠው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ጥርጣሬና አለመተማመን የሰፈነበት ትዳር አይሰምርም። ታዲያ አግባብነት የሌለው ቅናት ትዳራችሁን እንዳይበጠብጠው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ጓደኝነት ገደቡን ሲያልፍ

‘ከጓደኝነት ያለፈ ምንም ነገር የለንም’ ብላችሁ ታስባላችሁ? ይህ ዓይነቱ አመለካከት ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን መርምሩ።

መለያየት እና ፍቺ

ፍቺ በልጆች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

አንዳንድ ሰዎች፣ ወላጆች መፋታታቸው ለልጆች የተሻለ እንደሆነ ቢያስቡም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፍቺ በልጆች ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል።

በትዳር ደስታ ማጣት

የሞቀ ትዳር ውስጥ ሳይሆን እስር ቤት ውስጥ እንዳላችሁ ይሰማችኋል? ትዳራችሁ ደስታ የሰፈነበት እንዲሆን የሚረዷችሁ አምስት እርምጃዎች እነሆ!

የትዳር ጓደኛ ቢከዳም ደስተኛ ሕይወት መምራት ይቻላል?

የትዳር ጓደኛቸው ክህደት የፈጸመባቸው በርካታ ባለትዳሮች ከመጽሐፍ ቅዱስ መጽናኛ ማግኘት ችለዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ምንዝር ምን ይላል?

ምንዝር ለትዳር መፍረስ ምክንያት ይሆናል?

በትዳር ውስጥ የመተማመን ስሜትን እንደገና ማጎልበት

እንደ ምንዝር ያለ ከባድ ችግር በትዳራችሁ ውስጥ አጋጥሟችሁ ትዳራችሁን ለመታደግ እየጣራችሁ ከሆነ ተፈታታኝ ሁኔታ እንደሚያጋጥማችሁ ግልጽ ነው። ይሁንና ሊሳካላችሁ ይችላል!

መጽሐፍ ቅዱስ ፍቺን ይፈቅዳል?

ከዚህ ጋር በተያያዘ አምላክ የሚጠላው ምንድን ነው? የሚፈቅደውስ?

ፍቺ በስተርጅና—መከላከያው ምንድን ነው?

ሰዎች በስተርጅና የሚፋቱት ለምንድን ነው? የእናንተ ትዳር ተመሳሳይ ዕጣ እንዳይገጥመውስ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ፍቺ የሚያስከትለውን ጫና መቋቋም

አብዛኞቹ ፍቺ የፈጸሙ ሰዎች ሕይወታቸው ከጠበቁት በላይ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ጠቃሚ ምክር ይህንን ሁኔታ ለመቋቋም ይረዳል።

የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ፍቺ ምን አመለካከት አላቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች በትዳራቸው ውስጥ ችግር ለገጠማቸው ሰዎች እርዳታ ይሰጣሉ? አንድ የይሖዋ ምሥክር ፍቺ ለመፈጸም የጉባኤው ሽማግሌዎች ፈቃድ ያስፈልገዋል?