በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናትና በዚያ ላይ ለማሰላሰል ጊዜ መመደብ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ሰኔ 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

ንቁ! መጽሔትን ለማበርከትና ስጦታ ስለሆነው ሕይወት እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። የመግቢያ ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የይሖዋ ቃል አንድም ሳይቀር ይፈጸማል

ኤርምያስ፣ ባቢሎን ድል እንደምትደረግና ባድማ እንደምትሆን በዝርዝር የተናገረው ትንቢት አንድም ሳይቀር ተፈጽሟል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ በገባው ቃል ላይ ያለህ እምነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?

ኢያሱ፣ ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከሰጠው ተስፋ ውስጥ ሳይፈጸም የቀረ አንድም ቃል እንደሌለ አረጋግጧል። እኛስ አምላክ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

በትዕግሥት መጠባበቅ ለመጽናት ይረዳናል

ኤርምያስ ከባድ መከራ ቢደርስበትም አዎንታዊ አመለካከት ይዞ እንዲጸና የረዳው ምንድን ነው? ወደፊት ለሚያጋጥሙን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ሕዝቅኤል የአምላክን መልእክት ማወጅ ያስደስተው ነበር

ሕዝቅኤል፣ ይሖዋ አንድ ጥቅልል ሲሰጠው በራእይ ተመልክቷል፤ ከዚያም ጥቅልሉን እንዲበላው ይሖዋ ነግሮታል። ሕዝቅኤል ጥቅልሉን መብላቱ ምን ትርጉም ነበረው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ምሥራቹን በመስበክ ተደሰት

የአምላክን መንግሥት ምሥራች መስበክ አንዳንድ ጊዜ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፤ ይሁን እንጂ አምላክ በደስታ እንድናገለግለው ይፈልጋል። በስብከቱ ሥራችን መደሰት የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ከጥፋት ለመትረፍ ምልክት ይደረግብህ ይሆን?

ሕዝቅኤል የተመለከተው ራእይ የመጀመሪያ ፍጻሜውን ያገኘው የጥንቷ ኢየሩሳሌም ስትጠፋ ነው። ትንቢቱ በዘመናችን የሚኖረው ፍጻሜ እኛን የሚነካን እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የይሖዋን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ደግፉ

የይሖዋ አምላክን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች በድፍረት ልንደግፍ ይገባል። ይህን የምናደርገው እንዴት ነው? ይህን ማድረጋችን በጣም አስፈላጊ የሆነውስ ለምንድን ነው?