በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

የመግቢያ ናሙናዎች

የመግቢያ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

መግቢያ፦ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን ስለ አራቱ ፈረሰኞች የሚናገረውን ትንቢት ብዙዎች ያውቁታል። ይህ ትንቢት አንዳንዶችን ያስፈራቸዋል። ሌሎች ደግሞ ስለዚህ ትንቢት ይበልጥ ለማወቅ ይጓጓሉ።

ጥቅስ፦ ራእይ 1:3

አበርክት፦ ይህ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የአራቱ ፈረሰኞች ግልቢያ ወደፊት የተሻለ ጊዜ እንደሚመጣ የሚጠቁም ነው የምንለው ለምን እንደሆነ ያብራራል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ማወቅ የሚቻል ይመስልሃል?

ጥቅስ፦ ኢሳ 46:10

እውነት፦ አምላክ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ስለ ወደፊቱ ጊዜ ነግሮናል።

ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል!

መግቢያ፦ ቤተሰብን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ይህን አጭር ቪዲዮ ለሰዎች እያሳየን ነው። [ደስተኛ ቤተሰብ ሊኖርህ ይችላል! የተባለውን ብሮሹር ለማስተዋወቅ የተዘጋጀውን ቪዲዮ አጫውት።]

አበርክት፦ በቪዲዮው ላይ የተጠቀሰውን ብሮሹር ማንበብ የምትፈልግ ከሆነ ልሰጥህ እችላለሁ፤ አሊያም ደግሞ ከድረ ገጻችን ላይ እንዴት ማውረድ እንደምትችል ላሳይህ እችላለሁ።

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።