በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

በስዊዘርላንድ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሻቸውን ሲንከባከቡ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ግንቦት 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ መጽሔትን ለማበርከትና የወደፊቱን ጊዜ በተመለከተ እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

እስራኤል ዳግመኛ እንደምትቋቋም የሚያሳይ ምሳሌ

ይሖዋ አምላክ ነቢዩ ኤርምያስን መሬት እንዲገዛ ሲያዘው ምን ተስፋ ሰጥቶታል? ይሖዋ ጥሩነቱን ያሳየው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኤቤድሜሌክ ድፍረትና ደግነት በማሳየት ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቷል

ኤቤድሜሌክ ንጉሥ ሴዴቅያስ ፊት በቀረበበት ወቅት ድፍረት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዷል፤ የአምላክ ነቢይ ለሆነው ለኤርምያስ ደግሞ ደግነት አሳይቶታል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የአምልኮ ቦታዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ መያዝ

የአምልኮ ቦታዎቻችን በአምላክ ቅዱስ ስም የሚጠሩ እንደመሆናቸው መጠን በንጽሕናና በጥሩ ሁኔታ ሊያዙ ይገባል። የመንግሥት አዳራሻችንን በጥሩ ሁኔታ በመያዝ ረገድ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል

ነቢዩ ኤርምያስና ንጉሥ ሴዴቅያስ ከኢየሩሳሌም ጥፋት ጋር ተያይዘው የተጠቀሱ ቢሆንም ሁለቱ የገጠማቸው ዕጣ የተለያየ ነው።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም

ይሖዋ በዕድሜ በመግፋታቸው ምክንያት የቀድሞውን ያህል ማገልገል ያልቻሉትን ታማኝ አገልጋዮቹን እንዴት ይመለከታቸዋል?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን” አትፈልግ

ባሮክ ይሖዋን ያመልክና ኤርምያስን በታማኝነት ይረዳ የነበረ ቢሆንም በአንድ ወቅት ሚዛኑን ስቶ ነበር። ባሮክ በኢየሩሳሌም ላይ ከሚደርሰው ጥፋት ለመትረፍ ምን ማድረግ ነበረበት?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ ትሑታንን ይባርካል፤ እብሪተኞችን ደግሞ ይቀጣል

እብሪተኛዋ ባቢሎን በይሖዋ ሕዝቦች ላይ የጭካኔ ድርጊት ፈጽማለች። ንስሐ የገቡት እስራኤላውያን ከምርኮ ነፃ ወጥተዋል። ባቢሎንስ ምን ደረሰባት?