በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ  |  ነሐሴ 2017

ከነሐሴ 7-13

ሕዝቅኤል 28-31

ከነሐሴ 7-13
 • መዝሙር 136 እና ጸሎት

 • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

 • ይሖዋ አንድ አረማዊ ብሔር ላደረገው ነገር ወሮታ ከፍሏል”፦ (10 ደቂቃ)

  • ሕዝ 29:18—የባቢሎን ንጉሥ የሆነው ናቡከደነጾር ጢሮስን ለመያዝ ከፍተኛ ጥረት ያደረገ ቢሆንም ለድካሙ የተከፈለው ዋጋ የለም (it-2-E 1136 አን. 4)

  • ሕዝ 29:19—ንጉሥ ናቡከደነጾር በጢሮስ ላፈሰሰው ጉልበት ካሳ እንዲሆን የግብፅ ሀብት ተሰጥቶታል (it-1-E 698 አን. 5)

  • ሕዝ 29:20—ባቢሎናውያን የይሖዋን ዓላማ በማስፈጸማቸው ይሖዋ ዋጋ ከፍሏቸዋል (g86-E 11/8 27 አን. 4-5)

 • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

  • ሕዝ 28:12-19—የጢሮስ ገዢዎች የተከተሉት ጎዳና ሰይጣን ከተከተለው ጎዳና ጋር ተመሳሳይ የሆነው በምን መንገድ ነው? (it-2-E 604 አን. 4-5)

  • ሕዝ 30:13, 14—ይህ ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (w03 7/1 32 አን. 1-3)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

 • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ሕዝ 29:1-12

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

 • የዚህን ወር መግቢያዎች መዘጋጀት፦ (15 ደቂቃ) “የመግቢያ ናሙናዎች” በሚለው ርዕስ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የመግቢያ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። አስፋፊዎች በመግቢያቸው ላይ አንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮችን እንዲጠቅሱ እንዲሁም ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክቱ ምሥራች መስማት ትፈልጋለህ? የተባለውን ቪዲዮ እንዲያሳዩ አበረታታ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

 • መዝሙር 120

 • ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (5 ደቂቃ) አማራጭ፦ በዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። (yb17 35-36) አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።

 • አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—ትሕትና”፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ታማኝነትን የሚሸረሽሩ ነገሮችን አስወግዱ—ኩራት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።

 • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 13 አን. 24-32

 • ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)

 • መዝሙር 93 እና ጸሎት