በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

በአዘርባጃን ያሉ አስፋፊዎች ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ሲያበረክቱ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ነሐሴ 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

ንቁ! መጽሔትን ለማበርከትና አምላክ ሰዎችን የፈጠረው ለምን እንደሆነ እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ አንድ አረማዊ ብሔር ላደረገው ነገር ወሮታ ከፍሏል

ይሖዋ ባቢሎናውያን ጢሮስን ለ13 ዓመታት በመክበባቸው ወሮታ ከፍሏቸዋል፤ አንተስ በታማኝነት የምታከናውነውን ሥራና የምትከፍለውን መሥዋዕት ከፍ አድርጎ እንደሚመለከት የሚያሳየው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—ትሕትና

ትሕትና በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ትሕትና ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ጸሎትና ኢየሱስ የወውን ምሳሌ መከተል ትሕትና ለማዳበር የሚረዳን እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

አንድ ጠባቂ ያለበት ከባድ ኃላፊነት

አንድ ጠባቂ አደጋ መኖሩን ሲያይ ሕዝቡን የማስጠንቀቅ ኃላፊነት ነበረበት። ይሖዋ ሕዝቅኤልን በምሳሌያዊ ሁኔታ ለእስራኤል ቤት ጠባቂ አድርጎ ሲሾመው ምን እንዲያደርግ ይጠብቅበት ነበር?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የማጎጉ ጎግ በቅርቡ ይጠፋል

መጽሐፍ ቅዱስ ከማጎጉ ጎግ ጥፋት በፊትም ሆነ በኋላ የሚከናወኑ ነገሮችን ይናገራል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

አምላክን የሚያስደስቱ ባሕርያትን አዳብሩ—እምነት

ልክ እንደ አብርሃም እኛም በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ጭምር በይሖዋ አምላክ ላይ እምነት እንዳለን ማሳየት ይኖርብናል። ጠንካራ እምነትና ታማኝነትን ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ከፍ ያለ መሥፈርት እንዳለው ያስታውሰናል። ይህ ራእይ የሚያበረታታን እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በቅርቡ ረዳት አቅኚ መሆን የምችለው መቼ ነው?

የምስጋና መሥዋዕት ማቅረብ ከምንችልባቸው ጥሩ መንገዶች አንዱ ረዳት አቅኚ ሆኖ ማገልገል ነው። አንተስ በዚህ መንገድ በማገልገል አገልግሎትህን ማስፋት ትችላለህ?