በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ  |  ታኅሣሥ 2016

 ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ኢሳይያስ 1-5

‘ወደ ይሖዋ ተራራ እንውጣ’

‘ወደ ይሖዋ ተራራ እንውጣ’

2:2, 3

“በዘመኑ መጨረሻ”

አሁን የምንኖርበት ጊዜ

“የይሖዋ ቤት ተራራ”

ላቅ ያለው የይሖዋ ንጹሕ አምልኮ

“ብሔራትም ሁሉ ወደዚያ ይጎርፋሉ”

እውነተኛውን አምልኮ የተቀበሉ ሰዎች በአንድነት ይሰበሰባሉ

“ኑ፤ ወደ ይሖዋ ተራራ . . . እንውጣ”

እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች ሌሎችን ወደ ንጹሑ አምልኮ ይጋብዛሉ

“እሱ ስለ መንገዶቹ ያስተምረናል፤ በጎዳናዎቹም እንሄዳለን”

ይሖዋ በቃሉ አማካኝነት ይመራናል፤ እንዲሁም በመንገዱ እንድንሄድ ይረዳናል

2:4

“ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይማሩም”

 

“ሰይፋቸውን ማረሻ”

ማረሻ አፈሩን እየሰነጠቀ የሚሄድ የእርሻ መሣሪያ ነው። አንዳንድ ማረሻዎች የሚሠሩት ከብረት ነበር።—1ሳሙ 13:20

“ጦራቸውንም ማጭድ”

ማጭድ እጀታ ያለው ስለታም ብረት ነው። ይህ መሣሪያ የወይን ተክልን ለመግረዝ ያገለግል ነበር።—ኢሳ 18:5