በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ  |  ሚያዝያ 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

የመግቢያ ናሙናዎች

ንቁ!

ጥያቄ፦ በዛሬው ጊዜ እንደ አስማተኞች፣ ጠንቋዮችና ቫምፓየሮች ያሉ ምትሃታዊ ኃይል ያላቸው ገጸ ባሕርያትን የሚያሳዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እየተለመዱ መጥተዋል። እንዲህ ያለው መዝናኛ ጉዳት ያለው ይመስልሃል?

አበርክት፦ ይህ ንቁ! መጽሔት እንዲህ ያሉ መዝናኛዎች የብዙዎችን ቀልብ እየሳቡ ያሉት ለምን እንደሆነና እነዚህ መዝናኛዎች ምን ጉዳት እንዳላቸው ያብራራል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ የአምላክ መንግሥት በዓለም ላይ ላሉት ችግሮች መፍትሔ የሚያመጣው እንዴት ነው?

ጥቅስ፦ ማቴ 6:10

እውነት፦ የአምላክ መንግሥት በሰማይ ሰላም እንዲሰፍን አድርጓል፤ በምድርም ላይ ሰላም፣ ፍቅርና መረጋጋት እንዲሰፍን ያደርጋል።

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? (ተመላልሶ መጠየቅ)

ጥያቄ፦ [ቀጣይ ውይይት ለማድረግ በተዘጋጀው በትራክቱ ጀርባ ላይ ባለው ጥያቄ ላይ ትኩረት አድርግ።] በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ምን ዓይነት ሕይወት ይኖረናል?

ጥቅስ፦ መዝ 37:29፤ ኢሳ 65:21-23

አበርክት፦ [ምሥራች የተባለውን ብሮሹር አሳይ።] የዚህ ብሮሹር ትምህርት 7፣ እነዚህ ተስፋዎች ለእኛ ምን ትርጉም እንዳላቸው ይገልጻል። [ብሮሹሩን ተጠቅመህ ጥናት አስጀምር።]

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።