በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ከጉባኤ ርቃ የነበረች እህት ወደ ጉባኤ ስትመለስ ወንድሞች በደስታ ሲቀበሏት

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ሚያዝያ 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

ንቁ! መጽሔትን ለማበርከትና ስለ አምላክ መንግሥት እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ አስተሳሰብህንና ምግባርህን እንዲቀርጸው ፍቀድ

ታላቁ ሸክላ ሠሪ መንፈሳዊ ባሕርያችንን ይቀርጸዋል፤ ሆኖም እኛ ለመቀረጽ ፈቃደኛ መሆን አለብን።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጉላቸው

በስብሰባዎቻችን ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ክርስቲያናዊ ፍቅር በተግባር ሲገለጽ ማየትና እንዲህ ያለውን ፍቅር ማጣጣም አለበት። በጉባኤ ውስጥ ሞቅ ያለ የወዳጅነት መንፈስ እንዲሰፍን አስተዋጽኦ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋን የሚያውቅ ልብ አለህ?

በኤርምያስ ምዕራፍ 24 ላይ ይሖዋ አምላክ ሰዎችን ከበለስ ጋር አመሳስሏቸዋል። በጥሩ በለስ የተመሰሉት እነማን ናቸው? እኛስ እነሱ የተዉትን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የቀዘቀዙ ክርስቲያኖችን ማበረታታት ትችላላችሁ

የቀዘቀዙ ክርስቲያኖች በይሖዋ ዘንድ አሁንም ውድ ናቸው። ወደ ጉባኤ እንዲመለሱ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ልክ እንደ ኤርምያስ ደፋሮች ሁኑ

ኤርምያስ ኢየሩሳሌም ድምጥማጧ እንደሚጠፋ ትንቢት ተናግሯል። ደፋር ሆኖ እንዲቀጥል የረዳው ምንድን ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የመንግሥቱ መዝሙሮች ድፍረት ይሰጣሉ

በዛክሰንሃውዘን ማጎሪያ ካምፕ የነበሩ ወንድሞቻችን የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመራቸው ብርታት ሰጥቷቸዋል። እኛም ፈተና በሚያጋጥመን ወቅት እነዚህን መዝሙሮች መዘመራችን ድፍረት ይሰጠናል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ አዲሱ ቃል ኪዳን እንደሚቋቋም ትንቢት ተናግሯል

አዲሱን ቃል ኪዳን ከሕጉ ቃል ኪዳን የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው? አዲሱ ቃል ኪዳን ዘላቂ በረከት የሚያስገኘው እንዴት ነው?