በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

በአልባኒያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ሰዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኙ ሲጋብዙ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ መጋቢት 2017

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ መጽሔትን ለማበርከትና ስለ አምላክ መንግሥት እውነቱን ለማስተማር የተዘጋጁ የአቀራረብ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝ”

ይሖዋ አምላክ ኤርምያስን ነቢይ አድርጎ ሲሾመው ኤርምያስ ተልእኮውን ለመቀበል ብቁ እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበር። ይሖዋ ኤርምያስን ያበረታታው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ትተዋል

እስራኤላውያን በዘልማድ የሚያቀርቡት መሥዋዕት ለሚፈጽሙት ኃጢአት ማካካሻ እንደሚሆን ተሰምቷቸው ነበር። ኤርምያስ የእነዚህን ሰዎች ኃጢአትና ግብዝነት በድፍረት አጋልጧል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው? የተባለውን ብሮሹር መጠቀም

ይህን ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ስለ ይሖዋ ምሥክሮች፣ ስለ እንቅስቃሴያችን እንዲሁም ስለ ድርጅታችን እንዲማሩ ለመርዳት ተጠቀሙበት።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ሰዎች ሊሳካላቸው የሚችለው የይሖዋን አመራር እስከተከተሉ ድረስ ብቻ ነው

በጥንቷ እስራኤል የይሖዋን አመራር የተከተሉ ሰዎች ሰላም፣ ደስታና ብልጽግና አግኝተዋል

ክርስቲያናዊ ሕይወት

አምላክን ስማ የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት መንገድ

በደንብ ማንበብ ለማይችሉ ሰዎች መሠረታዊ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለማስተማር ሥዕሎቹንና ጥቅሶቹን ተጠቀም።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

እስራኤል ይሖዋን ረስቷል

ይሖዋ ኤርምያስ 500 ኪ.ሜ. ርቆ ወደሚገኘው ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ በመሄድ የተልባ እግር ቀበቶውን እዚያ እንዲደብቀው ያደረገው ለምንድን ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ቤተሰባችሁ ይሖዋን እንዳይረሳ እርዱ

ቋሚና ትርጉም ያለው የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራም ያላችሁ መሆኑ ቤተሰባችሁ ይሖዋን እንዳይረሳ ይረዳዋል። የቤተሰብ አምልኮ ፈታኝ እንዲሆን የሚያደርጉ ችግሮችን መወጣት የምትችሉት እንዴት ነው?