በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

በጣሊያን፣ ምሥራቹ ከቤት ወደ ቤት ሲሰበክ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ሐምሌ 2017

የመግቢያ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብን ለማበርከትና መከራ እንዲህ የበዛው ለምን እንደሆነ የሚገልጸውን እውነት ለማስተማር የተዘጋጁ የመግቢያ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን መግቢያ አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የሥጋ ልብ አለህ?

ከመዝናኛ፣ ከአለባበስና አጋጌጥ እንዲሁም ከፍቅርና ከይቅር ባይነት ጋር የተያያዙ ውሳኔዎችን ስናደርግ ልባችን ምን ሚና ይጫወታል? የሥጋ ልብ ሲባል ምን ማለት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

የገባኸውን ቃል ትጠብቃለህ?

ቃል ማፍረስ የሚያስከትለውን መዘዝ በተመለከተ ከንጉሥ ሴዴቅያስ ምን እንማራለን?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ይሖዋ ይቅር ሲለን በደላችንን አያስታውስም ማለት ነው?

ይሖዋ ይቅር ባይ እንደሆነ የሚያሳዩት የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎች ናቸው? ከዳዊት፣ ከምናሴና ከጴጥሮስ ጋር በተያያዘ ያደረገው ነገር ይቅር ባይ መሆኑን እንድንተማመን የሚያደርገን እንዴት ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ራስህን ይቅር ትላለህ?

ይሖዋ ከዚህ ቀደም የሠራናቸውን ስህተቶች ይቅር ቢለንም እኛ ግን ራሳችንን ይቅር ማለት ሊከብደን ይችላል። በዚህ ጊዜ ምን ሊረዳን ይችላል?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ንግሥና የሚገባው ሕጋዊ መብት ያለው ነው

ሕጋዊ መብት ያለውን ንጉሥ አስመልክቶ ሕዝቅኤል የተናገረው ትንቢት በኢየሱስ ላይ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? ይህስ ስለ ይሖዋ አምላክ ምን ያስተምረናል?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት

የቤቱ ባለቤት በሩን እስኪከፍትልን ስንጠብቅ የቤቱ ባለቤቶች እያዩን ወይም የምናወራውን እየሰሙ እንደሆነ ላናስተውል እንችላለን። ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

በጢሮስ ላይ የተነገረው ትንቢት በይሖዋ ቃል ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል

ሕዝቅኤል ጢሮስ እንደምትጠፋ የተናገረው ትንቢት አንድም ሳይቀር ተፈጽሟል።