እስራኤላውያን የዮርዳኖስን ወንዝ ከመሻገራቸው በፊት አቋማቸውን የሚፈትን ስውር የሆነ ፈተና አጋጥሟቸው ነበር። አንዳንዶቹ በአካባቢያቸው ካሉ ሞዓባውያን ጋር ስለተቀራረቡ መጥፎ ነገር እንዲፈጽሙ ለቀረበላቸው ፈተና ተሸንፈዋል። የእነዚህ እስራኤላውያን ታሪክ በዛሬው ጊዜ ለምንኖረው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ይሆንልናል።