በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ዘምሩ—አዲስ መዝሙሮች

 መዝሙር 149

ለቤዛው አመስጋኝ መሆን

ለቤዛው አመስጋኝ መሆን

አውርድ፦

(ሉቃስ 22:20)

 1. ይሖዋ ሆይ፣

  ባንተ ፊት መቆም ችለናል፤

  ከሁሉ የላቀ ፍቅር

  ስላሳየኸን።

  ልጅህን ላክህልን

  እንዲሆነን ቤዛ፤

  ሊኖር አይችልም

  ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ።

  (አዝማች)

  እኛን ሊያድን እሱ ሞተ፤

  ክቡር ደሙን ለኛ ሰጠ።

  ለዘላለም

  ልባዊ ምስጋና ይድረስ ላንተ።

 2. ኢየሱስ ቤዛችን የሆነው

  ፈቅዶ ነው፤

  ሕይወቱን እንዲሰጠን

  ፍቅር አነሳሳው።

  ማንም አልነበረም

  ከሞት ’ሚታደገን፤

  ልጅህ ደረሰልን

  አሁን ሕይወት አገኘን።

  (አዝማች)

  እኛን ሊያድን እሱ ሞተ፤

  ክቡር ደሙን ለኛ ሰጠ።

  ለዘላለም

  ልባዊ ምስጋና ይድረስ ላንተ።

(በተጨማሪም ዕብ. 9:13, 14ን እና 1 ጴጥ. 1:18, 19ን ተመልከት።)