በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ዘምሩ—አዲስ መዝሙሮች

 መዝሙር 142

ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መስበክ

ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መስበክ

አውርድ

(1 ጢሞቴዎስ 2:4)

 1. አምላክን መምሰል እንፈልጋለን፤

  እንደ’ሱ ከአድሎ እንርቃለን።

  ፈቃዱ ነው ሁሉም ዓይነት ሰዎች፣

  እንዲድኑ ሆነው የሱ ሕዝቦች።

  (አዝማች)

  ሰው ካለ ቦታ ’ንመርጥም፤

  ልብ እንጂ ፊት አናይም።

  ያምላክን መል’ክት ሁሉም ሰው ይስማ።

  ስለምናዝንላቸው፣

  ፈልገን ’ናስተምራቸው፤

  መዳን እንዲያገኝ ሁሉም ዓይነት ሰው።

 2. ለውጥ የለውም ’ሚገኙበት ቦታ፣

  መልካቸው፣ የፊታቸው ገጽታ።

  ቁም ነገሩ ልባቸው ብቻ ነው፤

  ውስጣቸውን ነው አምላክ የሚያየው።

  (አዝማች)

  ሰው ካለ ቦታ ’ንመርጥም፤

  ልብ እንጂ ፊት አናይም።

  ያምላክን መል’ክት ሁሉም ሰው ይስማ።

  ስለምናዝንላቸው፣

  ፈልገን ’ናስተምራቸው፤

  መዳን እንዲያገኝ ሁሉም ዓይነት ሰው።

 3. በምርጫቸው ይህን ዓለም ትተው፣

  ለሚመጡ ያምላክ እጅ ክፍት ነው።

  ስላወቅን ይህንን እውነታ፣

  እንሰብካለን ባገኘነው ቦታ።

  (አዝማች)

  ሰው ካለ ቦታ ’ንመርጥም፤

  ልብ እንጂ ፊት አናይም።

  ያምላክን መል’ክት ሁሉም ሰው ይስማ።

  ስለምናዝንላቸው፣

  ፈልገን ’ናስተምራቸው፤

  መዳን እንዲያገኝ ሁሉም ዓይነት ሰው።