በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ዘምሩ—አዲስ መዝሙሮች

 መዝሙር 138

ስምህ ይሖዋ ነው

ስምህ ይሖዋ ነው

አውርድ

(መዝሙር 83:18)

 1. የፍጥረታት ጌታ፣

  ሕያው ነህ፣ እውነተኛ።

  ለዘመናት የኖረው

  ስምህ ይሖዋ ነው።

  ሕዝብህ መሆናችን፣

  ክብር ነው ኩራታችን።

  እናውጅ ያንተን ግርማ፤

  ምድር ሁሉ ይስማ።

  (አዝማች)

  ይሖዋ፣ ይሖዋ

  የሚመስልህ የለም።

  በሰማይም፣ በምድርም

  ሌላ አምላክ የለም።

  ሁሉን ቻይ አንተ ብቻ ነህ፤

  ይህን ይወቅ ዓለም።

  ይሖዋ፣ ይሖዋ

  ሌላ አምላክ የለም ለኛ።

 2. እንደምትፈልገው፣

  ልብህ እንደሚመኘው፣

  እንድንሆን ታደርጋለህ፤

  ይሖዋ ነው ስምህ።

  ክቡር ስም ሰጠኸን፤

  ምሥክሮቼ አልከን።

  ‘ለስሜ የሚሆን ሕዝብ’

  ብለህ አከበርከን።

  (አዝማች)

  ይሖዋ፣ ይሖዋ

  የሚመስልህ የለም።

  በሰማይም፣ በምድርም

  ሌላ አምላክ የለም።

  ሁሉን ቻይ አንተ ብቻ ነህ፤

  ይህን ይወቅ ዓለም።

  ይሖዋ፣ ይሖዋ

  ሌላ አምላክ የለም ለኛ።

(በተጨማሪም 2 ዜና 6:14ን፣ መዝ. 72:19ን እና ኢሳ. 42:8ን ተመልከት።)