በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ዘምሩ—አዲስ መዝሙሮች

ይሖዋን ለማወደስና ለማምለክ የምንጠቀምባቸውን አዳዲስ መዝሙሮች አዳምጥ። ሙዚቃውንና ግጥሞቹን ካወረድክ በኋላ እነዚህን ግሩም መዝሙሮች ተለማመዳቸው።

በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ይምጣልን!

ይህ ግሩም መዝሙር፣ በክርስቶስ ኢየሱስ የሚመራውን የአምላክ መንግሥት በማቋቋሙ ይሖዋ አምላክን ለማመስገን የተዘጋጀ የውዳሴ መዝሙር ነው።

ድፍረት ስጠን

ይሖዋ ስለ ስሙ ስንመሠክር ድፍረት እንዲሰጠን የምናቀርበውን ልመና የያዘውን ይህን መዝሙር እንድትዘምር እንጋብዝሃለን።

ስምህ ይሖዋ ነው

የይሖዋን ክቡር ስም አወድሱ፤ እንዲሁም እሱ ሉዓላዊ አምላክ መሆኑን ለሰዎች ሁሉ ንገሩ።

ጸንተው እንዲቆሙ አስተምሯቸው

ይሖዋ አምላክ ጥበቃ እንዲያደርግልን እንዲሁም የሕይወትን ሩጫ በጽናት ለመጨረስ እንዲረዳን የቀረበ ልመና።

የአቅኚ ሕይወት

ለይሖዋ ያለህን ፍቅር እንዲሁም እሱ ስለሰጠህ የሚያረካ ሥራና አስደሳች ሕይወት የሚሰማህን ስሜት በመዝሙር ግለጽ።

ሰላም ወዳዶችን መፈለግ

ለሰዎች ፍቅር እንዳለን ብሎም የአምላክን ውድ በጎች ለማግኘት ትጋት የተሞላበት ፍለጋ እንደምናደርግ የሚገልጽ አስደሳች መዝሙር።

ለሁሉም ዓይነት ሰዎች መስበክ

ስለ ይሖዋ ጥሩነት ዘምር፤ እንዲሁም ሁሉም ዓይነት ሰዎች የእሱ ወዳጆች እንዲሆኑ የመርዳት መብት በማግኘትህ የሚሰማህን አድናቆት በመዝሙር ግለጽ።

በጨለማ ዓለም ውስጥ ብርሃን ማብራት

የምንሰብከው መልእክት ብሩህ ነው፤ በጨለማ ያበራል።

ስብከታችን ሰው ያድናል

ጊዜው ከማለቁ በፊት የአምላክን መልእክት ለሰዎች መስበክ አለብን።

ለአገልግሎት መዘጋጀት

ከሞቀ አልጋ ወጥቶ በቅዝቃዜ ማገልገል ከባድ ቢሆንም በዚህ ሁኔታ ለመስበክ ምን ማበረታቻ ማግኘት ይቻላል?

ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል

ኢየሱስ፣ ለተቀቡ ወንድሞቹ የሚደረገውን ማንኛውም እርዳታና ድጋፍ ለእሱ እንደተደረገ ይቆጥረዋል።

ልዩ ንብረት

ይሖዋ፣ በመንፈስ የተቀቡ ልጆቹን ይወዳቸዋል፤ እነሱም የእሱን ፈቃድ ማድረግ ያስደስታቸዋል።

አንድያ ልጅህን ሰጠኸን

እጅግ ውድ የሆነ ስጦታ ስለሰጠን ይሖዋ ይመስገን። ይህ ስጦታ ሁላችንም ተስፋ እንዲኖረን አድርጓል።

ለቤዛው አመስጋኝ መሆን

ኢየሱስ በፈቃደኝነት ለእኛ ሲል ሕይወቱን አሳልፎ መስጠቱ እስከ ዛሬ ከታዩት የፍቅር መግለጫዎች ሁሉ እጅግ የላቀ ነው እንድንል ያደርገናል፤ ይህ ስጦታ ይሖዋን ለዘላለም እንድናመሰግን ይገፋፋናል።

እገዛ የሚያስፈልጋቸውን መርዳት

ይሖዋን እሱ በሚፈልገው በማንኛውም መንገድ ማገልገል እንደሚያስደስትህ በመዝሙር ግለጽ።

የአምላክ ልጆች መገለጥ

ይሖዋ፣ የክርስቶስ ወንድሞችን ወደ ሰማይ የሚወስድበትንና ከክርስቶስ ጋር ድል የሚያደርጉበትን እንዲሁም አብረውት የሚነግሱበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።

ኃይላችን፣ ተስፋችን፣ ትምክህታችን

የሕይወት ውጣ ውረድ ሲከብደን አምላክ ኃይላችን፣ ተስፋችንና ትምክህታችን ነው።

ምን ይሰማሃል?

ቅኖችን ለመፈለግ የምትችለውን ሁሉ በማድረግህ ምን ተሰማህ?

ጸንተን እንጠብቃለን

በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥም ይሖዋን በታማኝነት እስከ መጨረሻው ማገልገላችንን እንድንቀጥል የሚረዳ መዝሙር።