በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 92

ለስምህ የሚሆን ቤት

ኦዲዮ ምረጥ
ለስምህ የሚሆን ቤት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(1 ዜና መዋዕል 29:16)

 1. 1. አምላክ ሆይ፣ ለስምህ ቤት መሥራት፣

  ክብር ነው የማይገኝ መብት!

  ይህን ቤት ሰጠንህ በደስታ፤

  ክብርህ ይናኝ በዚህ ቦታ።

  ላንተ ’ምንሰጥህ ሁሉም ነገር፣

  ቀድሞም ቢሆን ያንተ ነበር።

  ንብረት፣ ችሎታ፣ ኃይላችንን

  ሳንቆጥብ እንሰጥሃለን።

  (አዝማች)

  ይህን ቤት ላንተ ሰጠንህ፤

  እንዲጠራበት ስምህ።

  ለአገልግሎትህ ይዋል፤

  ተቀበለን እባክህ።

 2. 2. ይሖዋ ሆይ፣ እናወድስህ፤

  በክብርህ ይሞላ ቤትህ።

  ሕዝቦች ይምጡ፣ ይወቁ አንተን፤

  ግርማህም ይበልጥ ከፍ ይበል።

  ቤቱን ላምልኮህ ወስነናል፤

  መንከባከብ ይገባናል።

  ጸንቶ ’ንዲኖር እንመኛለን፤

  ድጋፍ ሆኖ ለሥራችን።

  (አዝማች)

  ይህን ቤት ላንተ ሰጠንህ፤

  እንዲጠራበት ስምህ።

  ለአገልግሎትህ ይዋል፤

  ተቀበለን እባክህ።

(በተጨማሪም 1 ነገ. 8:18, 27ን፣ 1 ዜና 29:11-14ን እና ሥራ 20:24ን ተመልከት።)