በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 87

ኑ! እረፍት አግኙ

ኦዲዮ ምረጥ
ኑ! እረፍት አግኙ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ዕብራውያን 10:24, 25)

 1. 1. የምንኖርበት ዓለም ብልሹ ነው፤

  ያምላክን መንገድ አያውቅም።

  አስተማማኝ መመሪያ ያስፈልጋል፤

  የራስ መንገድ አያዋጣም።

  ስብሰባዎቻችን ኃይል ያድሳሉ፤

  እምነት ያጠነክራሉ።

  ለመልካም ሥራ ያንቀሳቅሳሉ፤

  ለመበርታት ያስችላሉ።

  የይሖዋን ት’ዛዛት ቸል አንልም፤

  ፈቃዱን ማድረግ ’ንሻለን።

  ከስብሰባዎች መመሪያ ይገኛል፤

  ለ’ውነት ያለን ፍቅርም ያድጋል።

 2. 2. ይሖዋ ያውቃል የሚያስፈልገንን፤

  ምክሮቹን መስማት አለብን።

  ለስብሰባዎች ጊዜ መግዛታችን፣

  ያሳያል ጥበብ እንዳለን።

  የተሾሙ ወንዶች ’ሚያስተምሩን ቃል

  ያነሳሳናል ለተግባር።

  የወንድሞች ድጋፍ አይለየንም፤

  ብቻችንን አይደለንም።

  ለመኖር ከፈለግን ባዲስ ዓለም፣

  ስብሰባ መሄድ አንተውም።

  በስብሰባዎች ላይ እንማራለን፣

  ባምላክ ጥበብ መመራትን።

(በተጨማሪም መዝ. 37:18፤ 140:1ን፣ ምሳሌ 18:1ን፣ ኤፌ. 5:16ን እና ያዕ. 3:17ን ተመልከት።)