በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 82

“ብርሃናችሁ ይብራ”

ኦዲዮ ምረጥ
“ብርሃናችሁ ይብራ”
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 5:16)

 1. 1. “ያለም ብርሃን ናችሁ”

  ብሎናል ጌታ፤

  ብርሃናችን ይብራ

  ቀንና ማታ።

  የሰላም ምሥራች ይዟል

  ያምላክ ቃል፤

  ሰዎችን ስናስተምር

  ደምቆ ያበራል።

 2. 2. ምሥራቹ ብርሃን

  ይፈነጥቃል፤

  መል’ክቱ መነገር

  ይኖርበታል።

  ቃሉ ይመራናል

  ብርሃናችን ነው፤

  ሰዎች ብርሃኑን ይዩ

  እውነትን አውቀው።

 3. 3. መልካሙ ሥራችን

  ብርሃን ያበራል፤

  ለትምህርታችንም

  ውበት ይሰጣል።

  እንቀጥል ብርሃኑን

  ማብራታችንን፤

  ይህ ነው በይሖዋ ዘንድ

  የሚያስወድደን።

(በተጨማሪም መዝ. 119:130ን፣ ማቴ. 5:14, 15, 45ን እና ቆላ. 4:6ን ተመልከት።)