በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 64

በመከሩ ሥራ በደስታ መካፈል

ኦዲዮ ምረጥ
በመከሩ ሥራ በደስታ መካፈል
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ማቴዎስ 13:1-23)

 1. 1. ያለነው በመከር ወራት ነው፤

  ይህ ለኛ ታላቅ ክብር ነው።

  መከሩ ለአጨዳ ደርሷል፤

  ለኛም ድርሻ ተሰጥቶናል።

  ሥራውን እየመራ ያለው

  ምሳሌያችን ኢየሱስ ነው።

  ያገኘነው መብት እጅግ ታላቅ ነው፤

  በደስታ እንፈጽመው።

 2. 2. ለአምላክ፣ ለሰው ያለን ፍቅር፣

  እንድንተጋ ግድ ይለናል።

  የመከር ሥራው አስቸኳይ ነው፤

  የመጨረሻው ቀን ቀርቧል።

  ከአምላክ ጋር አብረን ስንሠራ

  ወደር የለውም ደስታችን።

  አምላክ በሰጠን ሥራ ከጸናን

  በረከት እናገኛለን።

(በተጨማሪም ማቴ. 24:13ን፣ 1 ቆሮ. 3:9ን እና 2 ጢሞ. 4:2ን ተመልከት።)