በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 61

እናንተ ምሥክሮች ወደፊት ግፉ!

ኦዲዮ ምረጥ
እናንተ ምሥክሮች ወደፊት ግፉ!
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሉቃስ 16:16)

 1. 1. እኛ የአምላክ ባሮች ደፋሮች ነን፤

  ለምሥራቹ ጥብቅና እንቆማለን።

  ሰይጣን ጥቃት ቢሰነዝርም፣

  ይሖዋ ከጎናችን ነው አንፈራም።

  (አዝማች)

  እናንተ ምሥክሮች ወደፊት ግፉ!

  ለአምላክ ሥራ በደስታ ተሰለፉ!

  አስታውቁ ምድር እንደምትሆን ገነት፤

  ይመጣል በቅርብ ብዙ በረከት።

 2. 2. የአምላክ አገልጋይ አይዘናጋም፤

  አይሞክርም ለማስደሰት ይህን ዓለም።

  ንጹሕ አቋሙን አያላላም፤

  ዓለም እንዲበክለውም አይፈቅድም።

  (አዝማች)

  እናንተ ምሥክሮች ወደፊት ግፉ!

  ለአምላክ ሥራ በደስታ ተሰለፉ!

  አስታውቁ ምድር እንደምትሆን ገነት፤

  ይመጣል በቅርብ ብዙ በረከት።

 3. 3. በአምላክ ተስፋ ሰዎች አፊዘዋል፤

  ቅዱስና ታላቅ ስሙንም ሰድበዋል።

  ስሙን እናስቀድስ ባንድነት፤

  ያለም ሕዝብ ይወቅ ያምላክን ማንነት።

  (አዝማች)

  እናንተ ምሥክሮች ወደፊት ግፉ!

  ለአምላክ ሥራ በደስታ ተሰለፉ!

  አስታውቁ ምድር እንደምትሆን ገነት፤

  ይመጣል በቅርብ ብዙ በረከት።

(በተጨማሪም ዘፀ. 9:16ን፣ ፊልጵ. 1:7ን፣ 2 ጢሞ. 2:3, 4ን እና ያዕ. 1:27ን ተመልከት።)