በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 53

ለአገልግሎት መዘጋጀት

ኦዲዮ ምረጥ
ለአገልግሎት መዘጋጀት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ኤርምያስ 1:17)

 1. 1. ሌሊቱ

  አልፎ ነግቷል፤

  ለስብከት ልንወጣ ነው።

  ግን ጨለማ ነው፤

  ማካፋት ጀምሯል።

  አያሰኝም ከአልጋ መውጣት፤

  ይበርዳል።

  (አዝማች)

  አዎንታዊ መሆን፣ ዝግጅት፣

  መጸለይ ለስኬት፤

  ብርታትና ጉልበት ይሰጣል፤

  ያጸናናል።

  ከኛ ጋር ናቸው መላእክቱ፤

  ’የሱስ አዟቸዋል።

  አብሮን ያለ ታማኝ ጓደኛም

  ያግዘናል።

 2.  2. ደስተኞች

  እንሆናለን፤

  ይህንን ካስታወስን።

  አለው ባምላክ ዘንድ

  ጥረታችን ዋጋ።

  ፍቅራችንን እንደማይረሳ

  አንዘንጋ።

  (አዝማች)

  አዎንታዊ መሆን፣ ዝግጅት፣

  መጸለይ ለስኬት፤

  ብርታትና ጉልበት ይሰጣል፤

  ያጸናናል።

  ከኛ ጋር ናቸው መላእክቱ፤

  ’የሱስ አዟቸዋል።

  አብሮን ያለ ታማኝ ጓደኛም

  ያግዘናል።

(በተጨማሪም መክ. 11:4ን፣ ማቴ. 10:5, 7ን፣ ሉቃስ 10:1ን እና ቲቶ 2:14ን ተመልከት።)