በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 42

የአምላክ አገልጋይ ጸሎት

ኦዲዮ ምረጥ
የአምላክ አገልጋይ ጸሎት
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ኤፌሶን 6:18)

 1. 1. ሉዓላዊው ይሖዋ አምላክ ሆይ፣

  ክቡር ስምህ የተቀደሰ ይሁን።

  ሁሉን ቻይ ነህ፤ ምን ይሳንሃል?

  ስለ መንግሥትህ እንጸልያለን።

  ያንተ መንግሥት ይምጣልን፤

  በረከት ያፍስስልን።

 2. 2. አባታችን፣ ምስጋና ይድረስህ፤

  ደግነትህ፣ ብዙ ነው በረከትህ።

  ሕይወትን፣ ብርሃንን ፈጥረሃል፤

  ጥበብ፣ ማስተዋል ካንተ ይገኛል።

  ይገባሃል ውዳሴ፤

  ’ናመስግንህ ሁልጊዜ።

 3. 3. የዚህ ዓለም መከራው ብዙ ነው፤

  መጽናኛ ግን ካንተ ነው ’ምናገኘው።

  ሸክማችንን ተቀበለን፤

  ጥንካሬ፣ ድፍረት ’ባክህ ስጠን።

  ታማኝ እንድንሆን እርዳን፤

  ልመናችንን ስማን።

(በተጨማሪም መዝ. 36:9፤ 50:14ን፣ ዮሐ. 16:33ን እና ያዕ. 1:5ን ተመልከት።)