በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 40

የማን ንብረት ነን?

ኦዲዮ ምረጥ
የማን ንብረት ነን?
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሮም 14:8)

 1. 1. ’ምትኖረው ለማን ነው?

  ማንን ነው ’ምታመልከው?

  ልትገዛለት የምትመርጠው፣

  ጌታህ ’ሚሆነው እሱ ነው።

  ለሁለት አማልክት

  ልብን ከፍሎ በመስጠት፣

  ሁለቱን መውደድ ስለማይቻል

  መወሰን ይገባሃል።

 2. 2. ’ምትኖረው ለማን ነው?

  ማንን ነው ’ምታመልከው?

  አንደኛው እውነት፣ ሌላው ሐሰት

  ናቸውና አንዱን ምረጥ።

  ታማኝ የምትሆነው

  ለዚህ ዓለም ቄሳር ነው?

  ወይስ ለእውነተኛው አምላክህ

  ዘወትር ትገዛለህ?

 3. 3. እኔ የምኖረው፣

  ሁሌም የምታዘዘው፣

  የተሳልኩትን ’ምፈጽመው

  ሰማይ ላለው አምላኬ ነው።

  በዋጋ ገዝቶኛል፤

  ታማኝ ልሆን ይገባል።

  መላ ሕይወቴን ሰጥቼዋለሁ፤

  ስሙን አወድሳለሁ።

(በተጨማሪም ኢያሱ 24:15ን፣ መዝ. 116:14, 18ን እና 2 ጢሞ. 2:19ን ተመልከት።)