በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 34

በንጹሕ አቋም መመላለስ

ኦዲዮ ምረጥ
በንጹሕ አቋም መመላለስ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 26)

 1. 1. አምላኬ ሆይ፣ ’ባክህ ፍረድልኝ፤

  ባንተ ታምኛለሁ፤ ንጹሕ አቋም አለኝ።

  ልቤን ከፍተህ ውስጤን ተመልከተኝ፤

  መጥፎ ነገር ቢገኝ እባክህ አጥራልኝ።

  (አዝማች)

  በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤

  በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።

 2. 2. ካታላይ ጋር አልቀራረብም፤

  ካስመሳዮችም ጋር አልተባበርም።

  ካመፀኞች ጋር አታጥፋ ነፍሴን፤

  ከግፈኞችም ጋር አታድርግ ዕጣዬን።

  (አዝማች)

  በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤

  በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።

 3. 3. ወድጃለሁ ያምልኮ ቤትህን፤

  የሙጥኝ ብያለሁ ንጹሕ አምልኮህን።

  መሠዊያህን በደስታ ’ዞራለሁ፤

  ምስጋናህን ሁሌ ለሰው አሰማለሁ።

  (አዝማች)

  በኔ በኩል ፍጹም ቆርጫለሁ፤

  በንጹሕ አቋሜ እመላለሳለሁ።

(በተጨማሪም መዝ. 25:2ን ተመልከት።)