በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 31

ከአምላክ ጋር ሂድ!

ኦዲዮ ምረጥ
ከአምላክ ጋር ሂድ!
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሚክያስ 6:8)

 1. 1. ካምላክ ጋር ሂድ ትሑት ሆነህ፤

  ታማኝ ፍቅር ይኑርህ።

  ካምላክ አትራቅ፤ ይሁን ወዳጅህ፤

  እሱ ነው ኃይል ’ሚሰጥህ።

  ያምላክን ቃል አጥብቀህ ያዘው፤

  አትታለል በሰው።

  ያምላክን እጅ አጥብቀህ ያዝ፤

  በታማኝነት ታዘዝ።

 2. 2. ካምላክ ጋር ሂድ ንጹሕ ሆነህ፤

  ከኃጢያት ድርጊት ርቀህ።

  ፈታኝ ሁኔታ ቢያጋጥምህም

  አምላክ አለ ከጎንህ።

  ምስጋና ’ሚገባውን ነገር፣

  እውነት የሆነውን፣

  እነዚ’ን ሁሌ አውጠንጥን፤

  አምላክ አብሮህ እንዲሆን።

 3. 3. ካምላክ ጋር ሂድ፤ ወዳጅህ ነው፤

  በደስታ አገልግለው።

  ስጦታው ብዙ፣ ወደር የሌለው፤

  ምንጊዜም አመስግነው።

  ይሖዋን ስታገለግለው

  ልብህ ደስ ይበለው።

  ደስታህን የሚያዩ ሁሉ

  የሱ ’ንደሆንክ ያውቃሉ።

(በተጨማሪም ዘፍ. 5:24፤ 6:9ን፣ ፊልጵ. 4:8ን እና 1 ጢሞ. 6:6-8ን ተመልከት።)