በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 23

ይሖዋ መግዛት ጀምሯል

ኦዲዮ ምረጥ
ይሖዋ መግዛት ጀምሯል
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ራእይ 11:15)

 1. 1. የአምላክ ልጅ ይወደስ፤

  መንግሥቱ ተቋቁሟል፤

  ከጽዮን ሆኖ መግዛት ጀምሯል።

  ከፍ እና’ርግ ድምፃችንን፤

  እንዘምር ላምላካችን።

  ዙፋኑን ይዟል

  ክርስቶስ አዳኛችን።

  (አዝማች)

  ምን ያመጣል የአምላክ መንግሥት?

  የጽድቅና የ’ውነትን ድል።

  ምን ያስገኛል የአምላክ መንግሥት?

  ሰላም፣ ደስታ፣ ፍጹም ሕይወት።

  ታማኝ ፍቅሩን ስላሳየን

  ይሖዋ ’ባት ይመስገን።

 2. 2. ክርስቶስ ሥልጣን ይዟል፤

  አርማጌዶንም ቀርቧል።

  የሰይጣን ዓለም በቅርብ ይጠፋል።

  ብዙዎች ስላልሰሙ

  ምሥራቹን አስፋፉ፤

  እርዷቸው ቅኖች

  ካምላክ ጎን ይሰለፉ።

  (አዝማች)

  ምን ያመጣል የአምላክ መንግሥት?

  የጽድቅና የ’ውነትን ድል።

  ምን ያስገኛል የአምላክ መንግሥት?

  ሰላም፣ ደስታ፣ ፍጹም ሕይወት።

  ታማኝ ፍቅሩን ስላሳየን

  ይሖዋ ’ባት ይመስገን።

 3.  3. ንጉሡን ’ናወድሰው፤

  ታላቅና ድንቅ ነው።

  በአምላክ ስም መጥቷል እናክብረው።

  ሁሉን የሚገዛበት ቀን

  በጣም በመቅረቡ፣

  ወዳምላክ ቤት ግቡ

  ሞገሱን ለምኑ።

  (አዝማች)

  ምን ያመጣል የአምላክ መንግሥት?

  የጽድቅና የ’ውነትን ድል።

  ምን ያስገኛል የአምላክ መንግሥት?

  ሰላም፣ ደስታ፣ ፍጹም ሕይወት።

  ታማኝ ፍቅሩን ስላሳየን

  ይሖዋ ’ባት ይመስገን።

(በተጨማሪም 2 ሳሙ. 7:22ን፣ ዳን. 2:44ን እና ራእይ 7:15ን ተመልከት።)