በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

ቋንቋ ምረጥ አማርኛ

 መዝሙር 147

የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተሰጥቶናል

ኦዲዮ ምረጥ
የዘላለም ሕይወት ተስፋ ተሰጥቶናል
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 37:29)

 1. 1. የዘላለም ሕይወት ተስፋ

  ለሰው ልጆች ተሰጥቷል።

  ‘ገሮች ምድርን ይወርሳሉ’፤

  ተስፋው ይፈጸማል።

  (አዝማች)

  የዘላለም ሕይወት

  ተስፋ ተሰጥቶናል።

  በ’ርግጥ ይፈጸማል፤

  አምላክ ቃል ገብቷል።

 2. 2. ምድር ገነት ትሆናለች፤

  ሰውም ፍጹም ይሆናል።

  ይሖዋ በምድራችን ላይ

  ሰላምን ያሰፍናል።

  (አዝማች)

  የዘላለም ሕይወት

  ተስፋ ተሰጥቶናል።

  በ’ርግጥ ይፈጸማል፤

  አምላክ ቃል ገብቷል።

 3. 3. በቅርብ ሙታን ይነሳሉ፤

  ያኔ ሐዘን ይረሳል።

  ይሖዋ በርኅራኄው

  እንባን ካይን ያብሳል።

  (አዝማች)

  የዘላለም ሕይወት

  ተስፋ ተሰጥቶናል።

  በ’ርግጥ ይፈጸማል፤

  አምላክ ቃል ገብቷል።

(በተጨማሪም ኢሳ. 25:8ን፣ ሉቃስ 23:43ን፣ ዮሐ. 11:25ን እና ራእይ 21:4ን ተመልከት።)