በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 142

ተስፋችንን አጥብቀን እንያዝ

ኦዲዮ ምረጥ
ተስፋችንን አጥብቀን እንያዝ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ዕብራውያን 6:18, 19)

 1. 1. የሰው ዘር በጨለማ ሲዳክር ኖሯል።

  ጥረቱም ነፋስን ማሳደድ ሆኗል።

  አንዱ ሌላውን ለማዳን አይችልም፣

  ኃጢያት ስላለባቸው ሁሉም።

  (አዝማች)

  ደስ ይበላችሁ፤ መንግሥቱ ቀርቧል!

  ጌታ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል።

  ክፋት ሁሉ በቅርቡ ይጠፋል፤

  ይህ ተስፋ መልሕቅ ሆኖ ያቆመናል።

 2. 2. “ያምላክ ቀን ቀርቧል!” ብሎ ማወጅ ይገባል፤

  “እስከ መቼ?” ብሎ መጮኽ ያበቃል!

  ፍጥረት ነፃ ይወጣል ከመቃተት፤

  ለአምላክ እንዘምር በግለት።

  (አዝማች)

  ደስ ይበላችሁ፤ መንግሥቱ ቀርቧል!

  ጌታ ከፍርሃት ነፃ ያወጣናል።

  ክፋት ሁሉ በቅርቡ ይጠፋል፤

  ይህ ተስፋ መልሕቅ ሆኖ ያቆመናል።

(በተጨማሪም መዝ. 27:14ን፣ መክ. 1:14ን፣ ኢዩ. 2:1ን፣ ዕን. 1:2, 3ን እና ሮም 8:22ን ተመልከት።)