በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 137

ታማኝ ሴቶች፣ ክርስቲያን እህቶች

ኦዲዮ ምረጥ
ታማኝ ሴቶች፣ ክርስቲያን እህቶች
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(ሮም 16:2)

 1. 1. ሣራና አስቴር፣ ማርያም፣ ሩት፣ ሌሎችም፣

  ጎበዝ ሴቶች፣ ታማኝ ሚስቶች ነበሩ፤

  ከምንም በላይ ለአምላክ ያደሩ።

  እነዚ’ን ታማኞች በስም አውቀናል፤

  ግን ስማቸው ባይሰፍርም በቃሉ፣

  ሞገሱን ያገኙ ብዙ ሴቶች አሉ።

 2. 2. ታማኞችና ደፋሮችም ናቸው፤

  ጥሩነትና ደግነት ያላቸው።

  መልካም ባሕርያቸው ነው መለያቸው።

  ጥሩ ምሳሌ ሆኑ ለሁሉም ሰው።

  እነሱን የምትመስሉ እህቶች፣

  መልካም ባሕርያችሁ ይጠቅማል ለሌሎች።

 3. 3. እናት፣ እህት፣ ሚስትና መበለቶች

  ድርሻቹን በደስታ ትወጣላችሁ።

  ልከኞች ናችሁ፣ ከልብ ’ምትገዙ፤

  አትፍሩ ሞገሱን ስላገኛችሁ።

  ውድ እህቶቻችን በሉ በርቱ፤

  ይሖዋ ያጽናችሁ፤ ቀርቧል ሽልማቱ።

(በተጨማሪም ፊልጵ. 4:3ን፣ 1 ጢሞ. 2:9, 10ን እና 1 ጴጥ. 3:4, 5ን ተመልከት።)