በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ንዑስ መምረጫው ሂድ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የይሖዋ ምሥክሮች

አማርኛ

ለይሖዋ ‘በደስታ ዘምሩ’

 መዝሙር 130

ይቅር ባይ ሁኑ

ኦዲዮ ምረጥ
ይቅር ባይ ሁኑ
እይታ
ጽሑፍ
ሥዕል

(መዝሙር 86:5)

 1. 1. ይሖዋ በፍቅሩ

  ተወዳጅ ልጁን ሰጠን።

  ኃጢያታችን እንዲሰረይ፣

  ድል እንዲነሳ ሞትን።

  ከልብ ንስሐ ከገባን፣

  ይቅርታ ’ናገኛለን፤

  በ’የሱስ ቤዛ በማመን

  ምሕረቱን ከለመንን።

 2. 2. ምሕረት ’ምናገኘው

  አምላክን ስንመስለው ነው፤

  በነፃ ይቅር በማለት፣

  ለሌላው ስናዝን ነው።

  ምሬትና ቂምን ትተን

  እንኑር ተቻችለን።

  ወንድሞችን ’ናክብራቸው፤

  እናሳይ ፍቅራችንን።

 3. 3. ተወዳጅ ነው ምሕረት፤

  ሁላችን እናዳብረው።

  ያርቀናል ከጥላቻ፤

  ቂም ከመያዝ በሌላው።

  ፍቅሩ ወደር የሌለውን

  አምላክን ከመሰልን፣

  እንደ ይሖዋ ’ባታችን

  ከልብ ይቅር ’ንላለን።

(በተጨማሪም ማቴ. 6:12ን፣ ኤፌ. 4:32ን እና ቆላ. 3:13ን ተመልከት።)